“የሀገር ህልውና ካስማ ፤በኪነ -ጥበባችን አርማ” ልዩ የኪነ-ጥበብ ምሽት በአቃቂ ቃሊቲ ======================== ግንቦት 10/2015 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ) “የሀገር ህልውና ካስማ ፤ በኪነ-ጥበባችን አርማ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስተባባሪነት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ ልዩ የኪነ-ጥበብ ፕሮግራም በደማቅ ሰነ- ስነ ስርዓት ማጠቃለያ መድረክ በአቃቂ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር በመካሄድ ላይ ነው። በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ደ/ር ሂሩት ካሳው ፣ የአቃቂ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ፣ የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መዝገበ ይስማውን ጨምሮ ሌሎች የክፍለ ከተማው አመራሮች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የኪነ- ጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተዋል ። Post navigation “እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የተዋበች ክ/ከተማ ካልፈጠርን የተዋበች አዲስ አበባን መፍጠር አንችልም!