ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን በማስመልከት የጸረ ሙስና ዘመቻ ንቅናቄ ተጀመረ።
ኅዳር 15/2015 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር “ሙስናን መታገል በተግባር” በሚል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ሳምንታዊ ንቅናቄ በፓናል ውይይት ዛሬ ተጀምሯል።
ሙስና ኃላፊነትን ወይም ስልጣንን በመጠቀም አድሏዊ በሆነ አሰራር የግል ጥቅምን በማካበት በሀገር እድገት ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ያደርሳል።
ነዋሪውን እያማረረ ያለው ሙስና ከንግግር ባለፈ አጥፊዎችን ሊያስተምር የሚችል ተግባራዊ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ያሉት ተሳታፊዎቹ በተለይ አመራሩ ሙስናን ለመታገል ቁርጠኛ ሊሆን ይገባል በማለት አቶ ዘነበ ወዬሳ ጠቁመዋል።
ውይይቱን የመሩት የክ/ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራ ኢንተረፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር እንደተናገሩት ሙስናን ለመከላከል በገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የምትገኙ ፈጻሚዎችና አስፈጻሚው አካላት ሚና የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የጸረ ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው አስተዳደር ስር የሚገኙ የመንግሰት ሰራተኞችና አመራሮች ፓናል ውይይት አካሄዷል ።