በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ አመራሮች “መሪነት እና በጎ-ፍቃደኝነት ለማህበራዊ መስተጋብር” በሚል መሪ ቃል ለ240 አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መረሃ-ግብር አካሄድ።
========================
መጋቢት 28/2015 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)
በማዕድ ማጋራት መረሃ-ግብሩ ላይ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ-አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ፣ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መዝገበ ይስማውን ጨምሮ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
በመረሃ-ግብሩ ላይ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ-ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሂሩት አለሜ ባደረጉት ንግግር “የዛሬውን የማዕድ ማጋራት ልዩ የሚያደርገው በጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ሃሳብ አመንጭነት የተጀመረውን የማዕድ ማጋራት ተግባራዊ ለማድረግ በክፍለ ከተማና በወረዳ የሚገኙ አመራሮች አንድ ሰው ለአንድ ቤተሰብ በሚል ሃሳብ ማዕድ ማጋራት ተችሏል” ብለዋል።
በዛሬው የማዕድ ማጋራት መረሃ-ግብር በክፍለ ከተማና በወረዳ የሚገኙ አመራሮች ከ700 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለ240 አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ለእያንዳንዳቸው 25ኪሎ ግራም ዱቄት፣ 3ሊት ዘይት እንዲሁም 1ኪሎ ቴምር ድጋፍ መደረጉን ኃላፊዋ አያይዘው ተናግረዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ-አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ በበኩላቸው በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት ዓላማ አድርጎ የተነሳ መረሃ-ግብር መሆኑን ገልፀው አመራሩም ከዋና ተግባሩ ጎን ለጎን ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን በተግባር ያሳየበት መረሃ-ግብር ነው ብለዋል።