የተከበራችሁ የክ/ከተማችን ነዋሪዎች

“እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ /ፋሲካ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉን ስናከብር በአብሮነት፣ ያለንን በጋራ በመቋደስ በፍፁም ኢትዮጵያዊነት ስሜት ሆነን እንድናከብር መልዕክቴን እያስተላለፍኩ፤ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የብልፅግና እና በረከት የምታተርፉበት ይሆንላችሁ ዘንድ እመኛለሁ።”

አበራ ብሩ (ዶ/ር)

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር

ዋና ሥራ አስፈፃሚ

ሚያዝያ 07/2015 ዓ.ም