#እንኳን ደስ አላችሁ!!
እኛ ኢትዮጵያዊያን ከተባበርንና ለጋራ ዓላማ ከተደመርን እንደምንችል በዛሬው የትውልድ አሻራ መርሃ ግብር በተግባር አሳይተናል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ የራሳችንን ሪከርድ በራሳችን እንስበር በሚል መርህ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዬን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ ሁሌም የሀገራቸውን ጥሪ በአንድነት ተቀብለው በትብብር በሚተገብሩ ውድ ልጆቿ ከ567 ሚሊዬን በላይ ችግኝ በመትከል ለተመዘገው አዲስ ሪከርድ በክ/ከተማችንም ከ641ሺ በላይ ችግኞችን በመትከል የትውልድ አሻራችንን በማሳረፋችን እንኳን ደስ አላችሁ!!
ይህ ውጤት እንዲመጣ፣ውጥናችን እንዲሰመር ሌት ከቀን የለፋችሁ ውድ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች፣የፀጥታ አካላት፣በመርሃ ግብሩ የተሳተፋችሁ የከተማና የፌደራል ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የክ/ከተማችን ነዋሪዎችና ወጣቶች በችግኝ በማፍላት፣በቁፋሮ፣በተከላው የተሳተፋችሁ በሙሉ የድካማችሁ ፍሬ አፍርቷል እና በብልፅግና ፓርቲ አመራር፣አባላት እና ደጋፊዎች ስም ምስጋናዬን እያቀረብኩ በቀጣይም የተከልናቸው ችግኞች ፍሬ እንዲያፈሩ በመንከባከብ ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንድንወጣ አሳስባለሁ።
አቶ መዝገቡ ይስማው
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ