#እንኳን ደስ አላችሁ አለን!!

==================

ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም(አቃቂ ቃሊቲ)

አረንጓዴ አሻራ የዘር፣ የሀይማኖት ፣ የብሔር ወይም የጾታ ጉዳይ ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ቤታችንን ኢትዮጵያ ለእኛ እና ለነገው አዲሱ ትውልድ ምቹ አድርገን የምናስተላልፍበት የኢትዮጵያዊነት ግዴታችን መሆኑን በመረዳት በዛሬው ዕለት ለተመዘገበው ሀገራዊ ድል የትውልድ አሻራችንን በማሳረፋችን እንኳን ደስ አላችሁ!!

ለተመዘገበው ሀገራዊ ስኬት ዝናቡና ብርዱ ሳይበግራችሁ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ችግኝ በመትከል የተሳተፋችሁ የተለያዩ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የክ/ከተማው ነዋሪዎች በአስተዳደሩ ስም ምስጋናዬን እያቀረብኩ የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ በማስቀጠል ኢትዮጽያን ወደ ልዕልና ማማ ከፍ ለማድረግ እያንዳንዳችን በተሰማራንበት የሥራ መስክ የራሳችንን ሪከርድ በመስበር የሀገርን ገጽታ ለመለወጥ ዛሬ ያሳየነውን አንድነትና ትብብር እንድናስቀጥል አሳስባለሁ።

ዶ/ር አበራ ብሩ

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ