የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል።

በስብሰባው ላይ በተለያዩ ሀገራዊ፣ፓርቲያዊ እንዲሁም ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቅ መክሮ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪ ወቅታዊ የሆኑ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት በመምከር የኢትዮጵያን ብልፅግና በህብረ ብሔራዊ አንድነት ለማረጋገጥ የሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የሚመክር ይሆናል።

ስብሰባው በቀጣይ ቀናትም የሚቀጥል ይሆናል።