የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በቴክኖሎጂ መገልገያ መሳሪያዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
========================
ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በክ/ከተማው ውስጥ ለሚገኙ ሴት የፅዳትና የጥበቃ ሰራተኞች በቴክኖሎጂ መገልገያ መሳሪያዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት የመሰረተ ልማት ቡድን መሪ ወ/ሮ ቤተልሔም ቶለሳ ስልጠና የሰጡ ሲሆን በስልጠናው የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ምንነት አገልግሎት ፣ አፀዳድ መደረግ የሚገባው ጥንቃቄ ፣ በጥንቃቄ ጉድለት የሚመጡ ችግሮችን የዳሰሰ ሲሆን በተጨማሪም የመስክ ምልከታ ተካሄዷል።
የጽ/ቤቱ ተወካይ አቶ ዬሴፍ አይተንፍሱ የፅዳትና ጥበቃ ስራ ለአንድ ተቋም ቁልፍ መሆኑንና ጠቁመው ስልጠናው በዋናነት ያስፈለገው የቴክኖሎጂ መገልገያ መሳሪያዎች ውድ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንቃቄና እንክብካቤ ስለሚያስፈልጋቸው መደረግ በሚያስፈልገው ጥንቃቄ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን ገልፀዋል።














