ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በጽ/ቤታቸው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ.ብሊንከንን ተቀብለው አነጋግረዋል።
ውይይታቸውም በተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ተስማምተዋል።
ኢትዮጵያ በሰላም ስምምነቱ ላይ እያስመዘገበች ያለችው ስኬት ተቀባይነት አግኝቷል።
በኢኮኖሚው፣ በልማት ጥረቶች፣ በተለይም በግብርና እና በቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ያሉ ጉዳዮችም ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል።
መጋቢት 06/2015 ዓ.ም


