1445ኛውን የኢድ-አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ የማጋራት መርሀ-ግብር ተካሄደ።
=========================
መጋቢት 26/2016 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባባሪያ ፅ/ቤት 1445ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ አነስተኛ ገቢ ላላቸው 500 የክ/ከተማው ነዋሪዎች ማዕድ የማጋራት መርሀ-ግብር አካሄዷል።
የክ/ከተማው የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባባሪያ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሂሩት አለሜ በዓሉ ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት የሰላምና የፍቅር ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመው መርሀ-ግብሩ እንዲሳካ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ኢድ-አልፈጥር በዓል የመረዳዳት ባህልን የሚጠናከርበት መሆኑን ገልፀው የማዕድ ማጋራቱ ዋና ዓላማ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ የሚሰጥ የፍቅር ስጦታ መሆኑንም ገልፀዋል።





