አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በኢትዮጲያ ዋና ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙት አስራ አንድ ክፍለ ከተሞች አንዱ ነው።በከተማው ደቡባዊ ክፍል ከከተማው መሃል 20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ብዙ ኢንደስትሪዎች ስለሚገኙ የኢንዱስትሪ ዞን ነው፤በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ 12 ወረዳዎች ያሉ ሲሆን በ2015 በጀት ዓመት መልሶ ማደራጀት በተሰራዉ መሠረት በስሩ 504 ብሎክ ፤በእማዉራ 18566 በአባዉራ 29272 በድምሩ 56379፤ በህዝብ ቁጥር 192859 ይገመታል ይገመታል።በደርግ ጊዜ የሰሜኑ ክፍል ቃሊቲ/ወረዳ 27/ ከፍትኛ 27 እና ደቡባዊው ክፍል አቃቂ/ወረዳ 26/ ከፍትኛ 26 ተብሎ ይጠራ ነበር።የክፍለ ከተማው ከፍታ ከ2050 እስከ 2331 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ሲሆን 281 ሜትር ርቀት አለው።ክፍለ ከተማው ስያሜውን ያገኘው አቃቂ እና ቃሊቲ የሚሉትን ስያሜዎች በማዋሃድ ነው።በአዲስ አበባ ደቡባዊ ክፍል ከምስራቅ እና ከደቡብ በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ፣ ከምዕራብ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ከሰሜን በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በቦሌ ክፍለ ከተሞች የተከበበ ነው።
ራዕይ
አዲስ አበባ ከተማ በ 2017 ዓ.ም በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ 5 ከተሞች መካከል አንዷ ሆና ማየት!
ተልዕኮ
አዲስ አበባ ከተማ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት የላቀ ልማት የሚረጋገጥባትና ጠንካራ የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ግንኙነት የሚጠናከርባት እና ለኗሪዎቿ ምቹ ከተማ ማድረግ!
እሴቶች
አድራሻ:-ቃሊቲ መናኸሪያ ፊለፊት.
ወረዳ 1
አቤሴሎም ድልድይ ፊት ለፊት እና ቃሊቲ ዓለም ባንክ መሄጃ መያክ ህንፃ ላይ
ስልክ ቁጥር:-0114-34-00-44
ወረዳ 2
አቃቂ መኮንን አሽዋ ፊት ለፊት እና ሮባ ህንፃ ላይ
ስልክ ቁጥር:-0118-42-01-40
ወረዳ 3
ከአፄ ቴዎድሮስ የመ/ደ ት/ ቤት ጀርባ ወይም የነገ ሰዉ ቴክኒክና ሙያ ካንፓስ አጠገብ
ስልክ ቁጥር:-0114-34-54-90
ወረዳ 4
ገላን ቁጥር 2 የመ/ደ ትምህርት ቤት ጀርባ
ስልክ ቁጥር:-0118-42-05-02
ወረዳ 5
ዉሃ ልማት አጠገብ
ስልክ ቁጥር:-0114-71-78-45
ወረዳ 6
ከ3F ፋብሪካ ፊት ለፊት እና ብሪጂስቶን ጎማ ፋብሪካ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር:-0114-70-73-39
ወረዳ 7
ቃሊቲ ገብርኤል አካባቢ/ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ጀርባ
ስልክ ቁጥር:-0114-71-79-31
ወረዳ 8
ቃሊቲ ቶታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር:-0114-34-26-10
ወረዳ 9
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ/ቅሊንጦ ማረሚያ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር:-
ወረዳ 10
ወደ ጎሮ መሄጃ ቀርሳ አደባባይ ፊት ለፊት/አይቲ ፓርክ አካባቢ
ስልክ ቁጥር:-
ወረዳ 12
ሳሎ የመ/ደ ትምህርት ቤት ጀርባ እና ገላን ኮንዶሚኒየም ህንፃ
ስልክ ቁጥር:-
ወረዳ 13
ቱሉዲምቱ ገብርዔል ቤ/ያን ፊትለፊት ያለው ህንፃ ላይ
ስልክ ቁጥር:-