ከጥር 01/2015 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የነበረውን ከመሬት ጋር የተያያዘ አገልግሎት አሰጣጥ በድጋሜ የተጀመረ መሆኑ ተገለጸ፡፡
=======================
መጋቢት 4/2015 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት ከስም ዝውውር እና ከመብት ፈጠራ (ሰነድ አልባ ይዞታዎች) በስተቀር ከዚህ በፊት ይሰጣቸው የነበሩ አገልግሎቶች በሙሉ መስጠት መጀመሩን በይፋ አስታውቋል፡፡
የአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት ከጥር 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ አቋርጦት የነበረውን ከመሬት ጋር የተያያዘ አገልግሎት በድጋሜ እየሰጠ ስለመሆኑ አገልግሎት ለማግኘት የመጡ ነዋሪዎች አረጋግጠውልናል፡፡
በጽ/ቤቱ አገልግሎት ለማግኘት ከመጡ ተገልጋዮች ተቋርጦ የነበረው ከመሬት ጋር የነበረው አገልግሎት በመጀመሩ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው ነገር ግን ከፍተኛ የተገላጋይ ቁጥር በመኖሩ መቸገራቸውን ተናግረው ጽ/ቤቱ ይህንን ተረድቶ መፍትሄ እንደሚሰጠው ያላቸውን ተስፋም ተናግረዋል፡፡
የአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት አቶ መኮንን ተረፈ በሰጡን መረጃ የካርታ ኮፒ፤ የባንክ እግድ፤ የፕላን ስምምነት፤ የፍርድ ቤት ማየት፤ የእድሳት ጥያቄዎች እና የመሳሰሉት አገልግሎቶች እየተሰጡ ሲሆን ቀድሞ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎቶች በሙሉ በቀጣይ እንደሚሰጥ አስገንዝበዋል፡፡
ሌላው የስም ዝውውር እና የመብት ፈጠራ ባለቤትነት አገልግሎቶች መስጠት እንዳልተጀመረ ነገር ግን የመብት ፈጠራ በአጭር ግዜ የሚጀመር ስለመሆኑ እና የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች ከሁለቱ የአገልግሎት ጥያቄዎች በስተቀር ማንኛውን ጥያቄዎቻቸውን መስጠት መጀመሩን አስረድተዋል፡፡
ከዚህ በፊት የተገላጋይን እንግልት ለመቀነስ ታሳቦ ለአገልግሎት አመቺነት የክፍለ ከተማው አስተዳደር በአካባቢ ከፋፍሎ እና በቀናት ፕሮግራም በማዘጋጀት የሚሰጠውን የአገልግሎት አስራር ሁኔታ አስቀርቶ በሳምንቱ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ከመሬት ጋር ያላቸውን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም አስረድተዋል፡፡




