የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ  ፅ/ቤት

በጽ/ቤቱ ስር ያሉ የስራ ሂደቶች 

  1. የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቡድን አስተባባሪ
  2. የሀብት ማሰባሰብና አቅም ማጎልበት ቡድን አስተባባሪ
  3. የሰላም እሴት ግንባታ ቡድን አስተባበሪ
  4. የአካባቢ መሰረተ ልማት ማስፋፋት ቡድን አስተባባሪ

ራዕይ/Vision

በ 2017 ዓ/ም የለማ የህብረተሰብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ተፈጥሮ ማየት፡፡

ተልዕኮ/Mision

በክፍለ ከተማው አስተዳደሩ ብሎክን ማዕከል ያደረገ የአግልግሎት አሰጣጥ፣ የመሠረተ ልማት፣ የፀጥታ ችግሮችን እና የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ፍላጎትን በመለየት የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት ችግሮችን ከምንጫቸው እንዲፈቱ በማድረግ የህብረተሰቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ፡፡

ዕሴቶች/Values

  • አሳታፊነት፡-
  • ሰብአዊነት፡-
  • ፍትሃዊነት፡-
  • ተጠያቂነት፡-
  • በዕውቀትና በእምነት መሥራት፡- 
  • ለለውጥ ዝግጁነት፡-
  • ጥራትና ወጪ ቆጣቢነት፡- 
  • ችግር ፈቺነት፡

አድራሻችን ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 207

የተቋሙ ዋና ዋና ተግባራት/አገልግሎቶች

  1. ጥናት ማካሄድ፤
  2. ፕሮጀክት ማበልጸግ እና ሀብት ማሰባሰብ፤
  3. የግንባታ ዲዛይን ማዘጋጀት፤
  4. የጨረታ ውለታ ማስተዳደር፤
  5. የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፤
  6. የሚገነቡ የመሰረተ ልማት ሥራዎች መረከብ/ ማስተዳደር፤
  7. የብሎክንና የመሰረተ ልማት መረጃን መሰብሰብና ማደራጀት፤
  8. በብሎክ የደንብ ጥሰት ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት እርምጃ እንዲወሰድ ማስደረግ፤
  9. የብሎክ አደረጃጀትን በመጠቀም ሰላምና ጸጥታን የተመለከተ ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ፤
  10. የብሎክ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል፤በህብረተሰብ ተሳትፎ የአካባቢን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ፤
  1. ለማህበረሰብ አቀፍ አደረጃጀቶች ንቅናቄ መፍጠር
  2. ለብሎክ ነዋሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት
  3. በብሎክ አደረጃጀት ላይ የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በመለየት ከሚመለከተው አካል ጋር እንዲፈታ ማመቻቸት፤
  4. የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማሰተባበር፤
  • የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ግንዛቤ እና ማስረፅ፤
  • የበጎ ፈቃድ ካውንስል ማሳተፍ፤
  • ለበጎ ፈቃድ የተሰበሰበውን ሀብት ማሰራጨት
  • በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዙሪያ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፤
  • እውቅናና ማበረታቻ መስጠት፤

ከተገልጋይ የሚጠበቁ/ማሟላት የሚገባቸው

  1. ጉዳያቸውን ከወረዳው አቅም በላይ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ከወረዳ ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
  2. በክፍለ ከተማው ነዋሪ መሆናቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ አለባቸው፡፡
  3. የግንባታ ስራ ተቋራጭ ማህበራት የተደራጁበትን መረጃ ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
  4. የግንባታ ስራ ተቋራጭ ማህበራት ስለመደራጀታው የሚገልጽ መረጃ ከወረዳ ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
  5. የግንባታ ስራ ተቋራጭ ማህበራት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
  6. ለመሰረተ ልማት ጨረታ ላይ ለመወዳደር የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግንባታ ፍቃድ ያስፈልጋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ የስጋት መረጃ ለመጠቆም ሲመጡ መታወቂያ መያዝ አለባቸው፡፡