በመንግስትና በግል አጋርነት (public privet partnership)100,000 ቤቶችን ለመገንባት ከቤት አልሚዎች ጋር ስምምነት ተፈረመ።

========================

መጋቢት 07/2015 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝቡን የቤት ጥያቄ ለመመለስ በመንግስትና በግል አጋርነት (public privet partnership)100.000 ቤቶችን ለመገንባት ከቤት አልማዎች ጋር ስምምነት ተፈረመ።

በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማ አስተዳደሩ የቤት ፍላጎት ለማሟላት በኮንዶሚኒየም ግንባታ፣ በቤት እድሳት እንዲሁም ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ቤቶችን በመገንባት ለነዋሪው ምቹ መኖሪያ አካባቢዎችን እየተፈጠረ ይገኛል ብለዋል።

በከተማችን ያለው ከፍተኛ የቤት ፍላጎት መንግስት ለማሟላት ብዙ ጥረት አድርጓል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመንግስት ብቻ ግን የቤት ፍላጎት ማሟላት ስለማይቻል የግሉ ዘርፍ በቤት ግንባታው እንዲስተፉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የቤት አቅርቦቱን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ዛሬ 100, 000 ቤቶችን በመንግስትና በግል አጋርነት (public privet partnership) 100,000 ቤቶችን ለመገንባት ከቤት አልሚዎች ጋር የተደረገው ስምምነት የዚሁ የትብብር ሥራ አንዱ አካል ነው።

የከተማው ነዋሪ የቤት ጥያቄ ለመፍታትም የተለያዩ አማራጮች በማቅረብ እየተሰራ ይገኛል :: ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው እንዲሰሩ እየተሰራ ነው ::

በሁሉም መስክ ተባብረን በጋራ ከሰራን የህዝባችን ጥያቄ መመለስ እንችላለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

በጥራት በፍጥናት ቤቶችን በመገንባት የነዋሪውን ፍላጐት ማሟላት እንድንችል ቤት አልሚዎች በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ አሳስበዋል።

በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደርጉት ቤት አልሚዎች እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ከከተማ አስዳደሩ ጋር በጋራ ለመገንባት የሰራው ሥራ አድንቀው ግንባታው በፍጥነትና በሃላፊነት እንደሚሰሩም ገልፀዋል::