የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንደሲትሪ ልማት  ፅ/ቤት

ራዕይ

አዲስ አበባ ከተማ በ2022 ምቹ የስራ ሁኔታ የተረጋገጠባት ዘላቂና አስተማማኝ የስራ እድል የፈጠሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች ያደጉባት ከተማ ሆና ማየት ነው፡፡

ተልዕኮ

የስራ ስምሪት አገልግሎትን በማስፋፋት፤ ሰላማዊ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነትን በማስፈን ለስራ ፈላጊው ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር፣የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በመተግበር ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ ነዋሪዎችን ኑሮ ማሻሻል እንዲሁም የመስሪያ ቦታ፣ የፋይናንስ፣ የካፒታል ሊዝ፣ የገበያ፣ ቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክና ምክር ድጋፍ በማድረግ ኢንተርፕራይዝና አምራች ኢንዱስትሪ በምርትና ምርታማነት ብቁና ተወደዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል፡፡

እሴቶች

  • ግልጽኝነት
  • ተጠያቂነት
  • ፍትሀዊነት
  • ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት
  • ለለውጥ ዝግጁነት
  • ስራ ፈጣሪነትን ማበረታታት
  • በእውቀት መምራት
  • የምርታማነት ባህል
  • አገልጋይነት
  • ታማኝነት

የጽ/ቤቱ ተገልጋዩች

  1. ስራ ፈላጊ የክ/ከተማዋ ነዋሪዎች
  2. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ የክ/ከተማዋ ነዋሪዎች
  3. የአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች
  4. የአሰሪና ሰራተኛ ወገኖች
  5. የአሰሪና ሰራተኛ ማህበራት
  6. በምግብ ዋስትና የታቀፋ የክ/ከተማዋ ነዋሪዎች
  7. የስራ ፈጠራ ባለቤቶች እና
  8. የአምራች ኢንዱስትሪ ባለሃብቶች ናቸው፡፡

የደንበኞች ግዴታ 

  • ትክክለኛ መረጃዎችን ማቅረብ
  • የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላትና ማቅረብ
  • በክትትልና ድጋፍ የሚሰጡ የማሻሻያ ግብኣቶችን ተግባራዊ ማድረግና
  • የአገልግሎት ሰጪ ተቋምን ህግና ስርኣት ማክበር ዋና ዋናዎቹ ናቸው