የወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት

 

ራዕይ (Vision) 

በ2017 ዓ.ም ተሳታፊና ተጠቃሚ የሆነ ወጣት፤ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ማየት፡፡

ተልዕኮ (Mission) 

ማዕከላትና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማስፋፋትና አቅማቸውን በማጎልበት፣ ህብረተሰቡን ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ የስፖርት ልማትን ማዘመን፡፡

እሴቶች (Values)

 ግልፀኝነት

  • አገልጋይነት
  • አሳታፊነት
  • ፍትሃዊነት
  • በቡድን መስራት
  • ማህበረሰባዊነት
  • ዝግጁነት
  • ተጠያቂነት

የስፖርት ተሳትፎና አካል ብቃት ቡድን ዋና ዋና ተግባራት / አገልግሎቶች/

  • ህብረተሰቡን በስፖርት ለሁሉምና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማሳተፍ
  • የትምህርት ቤቶች የስፖርት እንቅስቃሴ በቅንጅት እንደስፋፋና እንዲጠናከር ማድረግ
  • ህበረተሰቡን በመዝናኛ ስፖርቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ መፍጠር
  • ከወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ጋር በመቀናጀት የህብረተሰቡን የስፖርትና መዝናኛ ተሳትፎ ማረጋገጥ
  • የስፖርት ተሳትፎና መዝናኛ እንቅስቃሴ ድጋፍ፤ ክትትል እና ግምገማ ማድረግ

ተ.ቁ

ዋናዋና ተግባራት

ነባሩ የሥራ ሂደት

አዲሱ የሥራ ሂደት

1

ህብረተሰቡን በስፖርት ለሁሉምና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማሳተፍ

የብዙሃን ስፖርትና የአካልብቃት ስፖርት ያካተተ በጥናቱ ያካተተ አለመሆኑ

በተሸለ ድግግሞሽ በመፈጸም 95% ጥራቱንና ተደራሽነቱ የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጥ ተጠንቷል፡፡

2

የት/ቤቶች ስፖርት እንቅስቃሴ በቅንጅትእንዲስፋፋና እንዲጠናከር ማድረግ

የት/ቤቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በቅንጅትም ይሁን በተናጠል ለማስፋፋትም ይሁን ለማጠናክር በጥናቱ ያካተተ አለመሆኑ

በአዲሱ አሠራር 95% ጥራቱን የጠበቀ የት/ቤቶች ስፖርት እንቅስቃሴ በቅንጅት እንዲስፋፋና እንዲጠናከር አገልግሎት እንዲሰጥ በሚል ተጠንቷል፡፡

3

ህብረተሰቡ በመዝናኛ ስፖርቶች ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ መፍጠር

ምቹ የሆኑ የስፖርትና መዝናኛ ፕሮግራም እንዲዘጋጅ በጥናቱ አለመካተቱ

በአዲሱ አሠራር 95% ጥራቱን የጠበቀ የመዝናኛ ስፖርት ፕሮግራሞችና ምቹ ሁኔታዎ በመፍጠር አገልግሎት እንዲሰጥ በሚል ተጠንቷል፡፡

4

ከወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ጋር በመቀናጀትህብረተሰቡ የስፖርትና መዝናኛ ተሳትፎ ማረጋገጥ

የወጣት ስብእና መገንቢያ መዓከላት ስፖርት እና የመዝናኛ እንቅስቃሴ በቅንጅትም ይሁን በተናጠል ለማስፋፋትም ይሁን ለማጠናክር በጥናቱ ያካተተ አለመሆኑ

በአዲሱ አሠራር 95% ጥራቱን የጠበቀ የወጣት መዓከላት የስፖርትና የመዝናኛ እንቅስቃሴ በቅንጅት እንዲስፋፋና እንዲጠናከር አገልግሎት እንዲሰጥ በሚል ተጠንቷል፡፡

5

የስፖርት ተሳትፎና መዝናኛ እንቅስቃሴ ድጋፍ፣ ክትትል እናግምገማ ማድረግ

 

ድጋፍ ክትትል እና ግምገማ

ሂደቱ 32 ሰዓት ይፈጅ ነበር፡፡

በ32 ሰዓት ውስጥ 95% ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የክትትል፤  ድጋፍና ግምገማ ስርዓት እንዲዘረጋ ተቀርጿል፡፡