የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ድረስ ባለበት ይቀጥላል ተባለ።

=========================

መጋቢት 25/2015 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል ተወሰነ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ÷ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

#FBC