የአብሮነት፣ የርህራሄ፣ የመተሳሰብና የመረዳዳት መገለጫ የሆነው የታላቁ የረመዳን ፆምን አስመልክቶ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ደማቅ የኢፍጣር መርሀ -ግብር ተከናወነ ።
========================
ሚያዝያ 03/2015 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)
1444ኛው ታላቁ የረመዳን ፆምን አስመልክቶ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር “ኢፍጣራችን ለወገናችን ! ” በሚል መሪ ቃል ደማቅ የኢፍጣር መርሀ -ግብር ተከናውኗል ።
በመርሀ -ግብሩ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ፤ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጸሐፊ ሼህ ሁሴን በሽር፣ የክፍለ-ከተማው እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ኡስታዝ መሀመድን ጨምሮ የክፍለ ከተማውና የወረዳ እስልምና ጉ/ምክር ቤት አመራሮች፣ የከተማ እና የክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁሞ የተለያየ ሀይማኖት ተከታዮችም ተሳትፈዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ በመርሐ -ግብሩ ባደረጉት ንግግር የኢፍጣር ፕሮግራም ከሃይማኖታዊ አስተምህሮው ባሻገር የእርስ በርስ መተሳሰባችን፣ ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን፣ ፍቅራችንና አብሮነታችንን የበለጠ በማጠናከር ለሀገር ሰላምና እድገት በጋራ እንድንቆም የሚያነሳሳ ትልቅ ፋይዳ ያለው ፕሮግራም ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በቀጣይም በአላትን በጋራ የማክበር፣ የእርስ በርስ የመደጋገፍና የመተሳሰብ፤ አቅም የሌላቸው የተቸገሩ ወገኖች የማገዝ መልካም እሴቶች በየደረጃው ማሰቀጠል እንደሚገባ ዋና ስራ አስፈፃሚው አሳስበዋል።
በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጸሐፊ ሼህ ሁሴን በሽር በበኩላቸው “ኢፍጣራችን ለወገናችን ! ” በሚል መሪ ቃል መርሀ ግብሩን በደመቀ ስነ ስርዓት ላዘጋጀው የክ/ከተማው አስተዳደርና ላስተባበሩ አመራሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአብሮነት፣ የርህራሔ ፣ የመተሳሰብና የመረዳዳት መገለጫ የሆነው ታላቁ የረመዳን ፆምን አስመልክቶ በኢፍጣር ፕሮግራም አቅም ለሌላቸው ወገኖች መአድ በማጋርት ሙስሊሞች ምንም ዓይንት ልዩነት ሳይገድበን በአንድነት በፍቅር በመተሳሰብ እና በኢስላማዊ ስነምግባራችን ለሌሎችም ጭምር ዓርኣያ በመሆን፤ የእስልምና አስተምህሮን በመተግበር ለሃገራችን ሰላምና ዕድገት በጋራ አላህን የምንማጸንበት ሊሆን ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።