በ”ለነገዋ” የሴቶች የተሀድሶ እና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለሚገኙ ሰልጣኝ ሴቶች ሲሰጥ የቆየውን መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና ተጠናቀቀ።
========================
ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ታምራት ላቀው እንደገለፁት ጽ/ቤቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በ”ለነገዋ” የሴቶች የተሀድሶ እና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለሚገኙ ሰልጣኝ ሴቶች ለተከታታይ 3 ዙሮች ሲሰጥ የቆየውን መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና በዛሬው ዕለት መጠናቀቁን ገልጸዋል ።
ስልጠናው በወጣለት መርሀ -ግብር በተሳካ ሁኔታ መስጠት መቻሉም ተገልጿል ።



