ፋይናንስ ፅ/ቤት

በጽ/ቤቱ ሥር ያሉ ቡድኖች

  • የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን ስራዎች አሰተባባሪ
  • የግዥና ንብረት ኦዲትና ክትትል ቡድን
  • የኦዲትና ኢንስፔክሽን ቡደን
  • የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን
  • የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን

ራዕይ

በ2017 ዓ.ም የከተማ አስተዳደደሩን ሃብት በብቃት በማስተዳደርና ፈጣን ቀጣይነት ያለው ልማትን በማረጋጥ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ማምጣት

ተልዕኮ

ለከተማ ነዋሪ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ለማምጣት፣ የማህበረ – ኢኮኖሚ ጥናት በማከናወን ፣ የተቀናጀና ሁሉ አቀፍ  የልማት ዕቅድና በጀት በማዘጋጀት፣ ፍትሃዊ የበጀት ድልድል በማድረግ፣ የበጎ አድራጎትና ስነ ህዝብ ስራዎችን በማስተባበባር እና አፈፃፀማቸውን ተከታትሎ በመገምገም፣ ዘመናዊ ቀልጣፋና ውጤታማ የመንግስትፋይናንስ አስተዳደር ሰርዓት በመዘርጋትና የአስተዳደሩን ሀብት በአግባቡ ልማት ላይ እንዲውል በማድረግ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው  ልማትን ማረጋገጥ ነው፡፡

እሴቶች

  • ተጠያቂነት
  • ግልጽነት
  • የላቀ አገልግሎት እንሰጣለን
  • ለለውጥ ዝግጁ ነን
  • በዕውቀት በእምነት እንመራለን/በመመሪያ እንሰራለን
  • ለሀብት ውጤታማነት እንተጋለን
  • ለልማት ሥራዎች ዘላቂነት እንጥራለን



አድራሻችን

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሀንፃ 6ኛ ፎቅ

በጽ/ቤቱ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች

  • ከገቢ ሰብሳቢ መ/ቤቶች ገቢ በማጠቃለል ወደ ባንክ እናስገባለን
  • በተፈቀደው በጀት መሰረት የጥሬ ገንዘብ እቅድ እናዘጋጃለን
  • ደመወዝ፣ ለስራ ማስኬጃና የካፒታል በጀት ወጪ ጠይቀን በማምጣት ክፍያ እንፈጽማለን
  • ዘመናዊ ቀልጣፋና ውጤታማ የፋይናንስ አገልግሎት እንሰጣለን፤
  • የሂሳብ ሪፖርት በማጠቃለል ለሚመለከተው አካል ተደራሽ እናደርጋለን
  • ድጋፍና ክትትል በማድግ ግብረ መልስ እንሰጣለን ፣
  • የስልጠና ፍላጎት በማሰባሰብ ስልጠና እንሰጣለን
  • የእርዳታ ገንዘብ ( የጤና፣ሴፍትኔት፣ የመንግስት ወጪ አስተዳደር፣ የት/ቤቶች ድጎማ)ክፍያዎችን እንፈጽማለን
  • የባንክ አካውንት ለመክፈት ፣ለመዝጋት እና የፊርማ ናሙና ለማቀያየር ደብዳቤ እናዘጋጃለን
  • በየወሩ የክፍለ ከተማውን ሂሳብ በማጠቃለል እንዲዘጋ እናደርጋለን
  • የገቢ ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ተደራሽ እናደርጋለን

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ሟሟላት ያለባቸው ዝርዝር ሁኔታዎች

  • ትክክለኛ መረጃዎችን በወቅቱ የማቅረብ፣
  • የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎቸን የማሟላትና የማቅረብ ፣
  • በክትትልና ድጋፍ የሚሰጡ የማሻሻያ ገብዓቶችን ተግባራዊ የማድረግ ፣
  • የአገልግሎት ሰጪ ተቋምን ህግንና ሰርዓት የማክበር፤
  • የፋይናንስ ደንብና መመሪያን ማክበር