ፍትህ ፅ/ቤት

የስራ ሂደቶች

  • የህግ ጉዳዮች ክርክር ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ዐቃቤ ህግ
  • የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ዐቃቤ ህግ
  • የወንጄል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዐቃቤ ህግ

ራዕይ፡-(vision)

ክፍለ ከተማችን ፍትህ የሰፈነባት እና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ሆና ማየት፡፡

 

 

 

 

አድራሻ

  •  አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 3ኛ ፎቅ በስተ ቀኝ አቅጣጫ

 

 

ተልዕኮ

ለክፍለ ከተማችን ልማትና መልካም አስተዳደር መስፈን የሚያግዙ ህጎች እንዲወጡና ንቃተ ህግ እንዲፈጠር በማድረግ ተደራሽና የተቀላጠፈ የፍትህ አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠት የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡

እሴቶቻችን

  • ለተጠያቂነት እንሰራለን፡፡
  • በግልጽነት እንሰራለን፡፡
  • ለለዉጥ ዝግጁ እንሆናለን፡፡
  • የላቀ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
  • በእዉቀትና በእምነት እንመራለን፡፡
  • ለፍትህ እና ለህግ የበላይነት በፅናት እንታገላለን፡፡
  • ሌብነትን በፅናት እንታገላለን፡፡
  • መልካም የስራ ግንኙነት በመፍጠር ለጋራ አላማ እንቆማለን፡፡
  • ማንኛዉንም ተገልጋይ ማሰተናገድ የሚያሰችል ላይብራሪ እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል አለን

በተቋማችን የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • የክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና የህግ አማካሪ እና ወኪል ሆኖ ይሰራል፤
  • በፍትሐብሄር ጉዳዮች የከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪውን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ ማሳደግ፤
  • የወንጀል ሕግ አፈፃፀም ውጤታማነትን ማሳደግ፤
  • የከተማ አስተዳደሩን ነዋሪና አስፈፃሚ አካላት ንቃተ ሕግ ማሳደግ፤
  • አስተዳደራዊ ፍትህ እና የሕግ ኦዲት ውጤታማትን ማሳደግ፤
  • የሰብዓዊ መብት ማክበርና ማስከበር
  • የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል መከላከልን በማስተባበር ግንዛቤ ማሳደግ፣
  • በአገልግሎት አሰጣጥ አካታችነትን በማሳደግ አገልግሎት ፈልገው ወደ ዘርፉ የሚመጡ አቅመ-ደካማ ዜጎችን (አረጋዊያንን፣ የአካል ጉዳተኞችን፣ ሴቶችና ህጻናት) ቅድሚያ ሰጥቶ ማስተናገድ፣
  • የሰው ሃብት ማስፈፀም አቅም በማሳደግ በዕውቀት ፣በክህሎትና በመልካም በስነ-ምግባር የተሟላ ብቃት ያለው ሠራተኛ መገንባት፤

ከተገልጋይ የሚጠበቁ

  • በቂ ማስረጃዎችን ማደራጀትና በተገቢዉ ግዜ ለፍ/ጽ/ቤት በማቅረብ የፍትህ ስርአቱ በደንብ እንዲሳለጥ የበኩላቸዉን አሰተዋፆኦ በማድረግ ማገዝና ማጠናከር ይኖርባቸዋል፡፡