
በጽ/ቤቱን ስር ያሉ ስራ ቡድን
- የኅብረት ስራ ማህበራት ማደራጃና ማስፋፊያ ቡድን
- የኅብረት ስራ ማህበራት ግብይትና የገበያ መሰረተ ልማት ክትትል ቡድን
- የኅብረት ሥራ ማህበራት ፋይናንስ ሥራ አመራር ቡድን
- የኅብረት ስራ ማህበራት ኢንስፔክሽንና ህግ አገልግሎት ቡድን
- የኅብረት ስራ ማህበራት ኦዲት ቡድን
ራዕይ
በ2022 ዓ.ም የአባላትን ኑሮ በላቀ ደረጃ የለወጡ እና ለአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ከፍተኛ ሚና የሚያበረክቱ ጠንካራና ተወዳዳሪ ኅብረት ሥራ ማኅበራትን መፍጠር ነው፡፡
እሴቶች
- ግልጽነት
- ተጠያቂነት
- ፍትሀዊነትና አሳታፊነት
- ታማኝነት
- ለሌሎች ማሰብ
- መተባበርና መቀናጀት
- በህብረት ስራ ማመን
- የማያቋርጥ የለውጥ ባህል
ተልዕኮ
”የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የአካባቢውን ሃብት መሰረት አድርጎ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሩን ለመፍታት በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ በተለያየ አይነትና ደረጃ የኅብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት፣ በማጠናከርና በማዘመን፣ አቅማቸውን በመገንባት፣ የግብይት ተሳትፎአቸውን እና ድርሻቸውን በማሳደግ፤ ምርታማነታቸውን በመጨመር፣የቁጠባ ባህልን በማሳደግ፣ የማበደርና የመበደር አቅም በመፍጠርና ኢንቨስትመንትን በማሳደግ፤ ህግና ህጋዊነታቸውን በማስጠበቅ የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ቀልጣፋ እና የአባላትን ተጠቃሚነት በዘላቂነት ያረጋገጡ ውጤታማና ተወዳዳሪ የኅብረት ስራ ማህበራትን መፍጠር፡፡”
አድራሻችን
አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ——-505
በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች ብዛትና ዝርዝር ከተቻለ የመፈፀሚያ ስታንደርድ ያለው
ስታንደርድ/በሰዓት 1. የማደራጀት አገልግሎት——————————————————— 200 2. የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት አገልግሎት ——————-‹ 58 3. ለኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደረግ ክትትልና ድጋፍ አገልግሎት 4. የሂሳብ ክትትልና ድጋፍ አገልግሎት፣ 28 5. የስልጠና አገልግሎት 452 6. የጥናት አገልግሎት 680 7. የመረጃ አገልግሎት 384 8. የፕሮጀክት ዝግጅት አገልግሎት 9. የህብረት ስራ ማህበራት ፈንድ የማቋቋምና ድጋፍ አገልግሎት 10. የግብይት መረጃ አገልግሎት – 140 11. የግብይት ዳሰሳ ጥናት አገልግሎት 352 12. የግብይት መሠረተ ልማት ማመቻቸት፣ ማሻሻልና ማዘመን ድጋፍ አገልግሎት…..72 13. የተቋማት አጠቃቀም ድጋፍ አገልግሎት 108 14. ምርትና አገልግሎትን የማስተዋወቅ ድጋፍ 144 15. የግብይት ብድር ማመቻቸት ድጋፍ አገልግሎት 128 16. የገበያ ትስስር ድጋፍ አገልግሎት 64 17. የብድር ትስስርና ድጋፍ አገልግሎት 224 18. የኢንሹራስ ትስስርና ድጋፍ አገልግሎት 248 19. የቁጠባ ባህል እንዲዳብር ማድረግ 620 20. የቁጠባና ብድር ስርአትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ የማድረግ የድጋፍ አገልግሎት 469 21. የኢንስፔክሽን አገልግሎት 24 22. የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ———————————————— 51 23. የሽምግልና ዳኝነት አገልግሎት —————————————- 46 24. ህብረት ስራ ማህበራትን የብቃት ደረጃ ማውጣት አገልግሎት ———— 35 25. የዕውቅና ሰርተፍኬት የመስጠት አገልግሎት —————————– 152 26. በብቃት ማረጋገጥ ወቅት የሚነሱ ቅሬታዎችን መፍታት 27. የኦዲት አገልግሎት ————————————————————— 144 ለመሠረታዊ ሸማች ——————————————————————160 ለመሠረታዉ ገንዘብ ቁጠባ ———————————————————— 56 28. የኦዲት አፈጻጸም አገልግሎት ——————————————————– 144
|
ከተገልጋይ የሚጠበቅ ሟሟላት ያለባቸው ዝርዝር ሁኔታዎች
የተናጠል ካርታ ለመውሰድ ተገልጋይ ሟሟላት ያለበት መስፈርት 1. የማህበሩ ሊቀመንበር የተናጠል ካርታ እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ ደብዳቤ 2.የማህበሩ አባላት 2/3ተኛ የተናጠል ካርታ እንዲሰጣቸው የተፈራረሙበት ቃለ ጉባኤ 3. የዘመኑንግብርስለመክፈላቸውየሚያሳይመረጃ 4.የሽንሻኖ ክፍፍል ቃለ ጉባኤ እና ካርታ ኮፒ 5.የዘመኑ ሊዝ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ የማህበሩ ማህተም ያለው 6.መሰረት ማለቁን የሚያረጋግጥ ማስረጃ /ከግንባታፈቃድ ጽ/ቤት/ የመተካካት መስፈርቶች በመኖሪያ ቤት ህ/ስራ ማህበራት የአፈጻጸም መመሪያ 7/2003 ዓ.ም መሰረት 1.የአዲሱ አባል የአባልነት ጥያቄና 2/3 ተኛው የማህበሩ አባላት አዲስን አባል የተቀበሉበት ማረጋገጫ ቃለ ጉባኤ 2. ነባሩ አባል የስንብት ጥያቄ ማመልከቻና 2/3ተኛው የማህበሩ አባላት ስንብቱን ሲያጸድቁ 3. ተሰናባቹ አባል ጥቅሙ እንደ ተከበረለት የሚያሳይ መረጃ (ስምምነት) 4.የተሰናባቹ አባል የትዳር ጓደኛ የስምምነት ፍርማ (ከመታወቂያ ጋር በአካል በመገኘት) 5. ተሰናባቹ አባል የትዳር ጓደኛ ከሌለው ከሚመለከተው አካል የታደሰ ያላገባ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
|
ከተገልጋይ የሚጠበቅ ሟሟላት ያለባቸው ዝርዝር ሁኔታዎች
- ማንኛውም ኅብረት ሥራ ማኅበር አግባብ ባለው ባለሥልጣን መመዝገብ አለበት፡፡ ማንኛውም ማኅበር፣ የኅብረት ሥራ ማኅበር ሆኖ ለመመዝገብ ማመልከቻውን ከሚከተሉት ጋር አያይዞ አግባብ ላለው ባለሥልጣን ያቀርባል
- የመሥራቾች ስብሰባ ቃለ ጉባኤ
- የኅብረት ሥራ ማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ሦስት ቅጂዎች
- የኅብረት ሥራ ማኅበሩን የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት ስም፣ አድራሻና ፊርማ፤
- የኅብረት ሥራ ማህበሩን የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ስም፣ አድራሻና ፊርማ፤
- የኅብረት ሥራ ማኅበር አባላት ሆነው የሚመዘገቡት ግለሰቦች
- የኅብረት ሥራ ማህበሩ ከመሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር በላይ ከሆነ የአባል ኅብረት ሥራ ማህበራትን አድራሻ እና የተወካዮች ፊርማ፤
- ከሦስት እስከ አምሰት ዓመት የሚደረስ የኅበረት ሥራ ማህበሩ የሥራ ዕቅድ፤ሰነድ፤
- የመነሻ ካፒታሉን መጠንና ተሰብስቦ በባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጉን
- የመነሻ ካፒታሉን መጠንና ተሰብስቦ በባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጉን ወይም ባንክ በሌለበት አካባቢ ከሆነ መዝጋቢው በወሰነው የፋይናንስ ተቋማት መቀመጡን የሚያረጋግጥ
- ማኅበሩ የሚሠራበት ቦታ መግለጫ፤
- 985/2009 አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጡ ደንቦች ወይም መመሪያዎች የሚወሰኑ ሌሎች መግለጫዎች፡፡