የባህል፤ኪነጥበብና ቱሪዝም ፅ/ቤት

በጽ/ቤቱ ስር ያሉ ቡድኖች

  • የቱሪዝም ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ቡድን
  • የኪነ ጥበብ ሀብቶች ልማት መድረኮች እና ኩነቶች ዝግጅት ቡድን
  • ቤተ መፃህፍት አገልግሎት አሰጣጥ ቡድን
  • የኪነ-ጥበብ ኢንዱስትሪ ማበልጸግና ማስፋፋት ቡድን
  • የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ብቃት ማረጋገጥ ቡድን
  • የባህል እሴት እደጥበብ ሀብቶች ልማት ቡድን

ራዕይ (Vision)

የክ/ከተማችንን ሕዝብ ባህላዊ፣ ኪነ ጥበባዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ መስህቦችን በማጥናት፣ በመጠበቅ፣ በማልማት፣ በማስተዋወቅና ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ እና የክ/ከተማችንን መልካም ገጽታ በመገንባት ዘላቂ የሆነ ፣ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ፣

ተልዕኮ (Mission)

በ2022 የባህል፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ዘርፍን በማላቅ ከቀዳሚ የክ/ከተማችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና መሠረቶች አንዱ ማድረግ

እሴቶች (Values)

  • ብዝሀነትን ማክበር
  • እንግዳ ተቀባይነት
  • ግልጸነት
  • ተጠያቂነት
  • ለለውጥ ዝግጁነት
  • የላቀ አገልግሎት
  • አሳታፊነት
  • ሙያዊ ብቃትን ማሳደግ

 

አድራሻ

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንጻ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር ……..

የጽ/ቤቱ ዋና ዋና  አገልግሎቶች

በባህል ዘርፍ፤ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ዘርፍ

  1. የባህል አገልግሎቶች የሙያ ብቃት(ማረጋገጥ/ጫ) መስጠት ፣ ማደስ ፣ቁጥጥርና ክትትል ስርዓት መዘርጋት፣
  2. የባህል እሴቶችን የማሳደግ፣ የማስተዋወቅና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን፣እንዲሁም መጤ ባህሎችን የመከላከል አገልግሎት፣(መስጠት)
  3. ከባህል ዕደ-ጥበቦች አንጻር አገራችን ከዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንድታገኝና በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎችም ገቢ እንዲያገኙ፤ እንዲሁም ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር ስልጠና የማመቻቸትና የማስተዋወቅ ተያያዥነት ያላቸውን አገልግሎቶች መስጠት፣
  4. በከተማችን የሚገኙ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ማጥናት፣ ማልማት፣ መንከባከብና እድሳት እንዲያገኙ ማድረግ፤እንዲሁም የምዝገባ ስርአት መዘርጋት ፡፡
  5. አዲስ አበባ ከተማን የቱሪዝም መዳረሻ ከማድረግ አንጻር የቱሪስት መስህቦችን ማልማትና እንዲሁም በከተማው ውስጥ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ፤ብሎም ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን ማረጋገጥ፡፡
  6. ለቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሙያ ብቃት(ማረጋገጥ/ጫ) መስጠት፣ ማደስ፣ በአገልግሎቶች አሰጣጥ ላይ የቁጥጥርና ክትትል ስርአት በመዘርጋት የአገልግሎቱ ጥራትና ተደራሽነትን፣ ህጋዊነትን ማረጋገጥ፡፡
  7. ከተንቀሳቃሽ ቅርሶችና ከሙዚየም ጋር በተያያዘ ለታሪክ አጥኚዎችና ለጎብኚዎች አገልግሎት መስጠት፡፡
  8. ለተማሪዎች ብሎም ለከተማዋ ነዋሪዎች፣ የቤተ መፃህፍት የንባብ ፣ የውሰትና የሪፈረንስ አገልግሎት መስጠት አገልግሎቱንም በማዘመን በአይ.ሲ.ቲ የታገዘ ማድረግ/አገልግሎት መስጠት፡፡
  9. ለከፍተኛ አመራሮችና በተለያየ እርከን ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች የልዩ ቤተመፃህፍት አገልግሎት መስጠት፡፡ይኸውም የንባብ ፣ የውሰትና የሪፈረንስ አገልግሎት፤በሌላ መልኩም ከአመራሩ ጋር አብሮ የሚሄድ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ማድረግ፡፡
  10. የሴቶችንና፣ ወጣቶችን ፖለቲካዊ፤ኢኮኖሚያዊና፣ ማህበራዊ ተጠቃሚነትን

    የሚያረጋግጡ የኪነ-ጥበብ ውጤቶችን በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፡፡

  1. ህፃናትን የሚገነቡና ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያስችሉ፤የኪነ-ጥበብ ውጤቶችን በማዘጋጀት ለተገልጋዩ ተደራሽ ማድረግ፡፡

  በኪነ-ጥበብ ዘርፍ የሚካተቱ አገልግሎቶች፤

  1. የኪነ-ጥበብ ክበብ ማደራጀት ስራ መስራት፣
  2. በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት ሙያዊ ሥልጠና መስጠት፣
  3. የኪነ-ጥበብ አዲስ የብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠት፣
  4. የኪነ-ጥበብ የሙያ ብቃት እድሳት አገልግሎት መስጠት፣
  5. የተደራሽ የኪነ-ጥበብ መረጃዎችን አገልግሎት መስጠት፣
  6. የኪነ-ጥበባት የሱፐርቪዥን አገልግሎት መስጠት፣
  7. የኪነ-ጥበብ ከተማ አቀፍ ኩነቶችን ማስተባበር አገልግሎት መስጠት፣
  8. የስነ-ጽሁፍ ምሽት አገልግሎት መስጠት፣
  9. የኪነ-ጥበብ የዕይታዊ ጥበባት ኤግዚቪሽን ማዘጋጀት፣

በቱሪዝም ዘርፍ የሚካተቱ አገልግሎቶች፣                     

  1. የቱሪዝም አገልግሎቶች፣ ገበያ ጥናት (መስህቦችን፣ አገልግሎቶችን ማጥናት መረጃዎችን የማቅረብ አገልግሎት መስጠት፣
  2. የከተማውን የቱሪዝም ስታስቲክስ በመሰብሰብ፣ በመተንተን፣ በማደራጀት የመረጃ አገልግሎት መስጠት፣
  3. የከተማውን የቱሪዝም ሀብቶች በህትመትና በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ማሰራጨትና ማስተዋወቅ፣
  4. የከተማውን የቱሪዝም ሀብቶች በተለያዩ ኤግዚቪሽን ላይ በማሳተፍ ማስተዋወቅና የቱሪዝም ገበያ ሲምፖዚየም ማዘጋጀትና ገበያ መፍጠር፣