የምግብ መዳኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ፅ/ቤት

በጽ/ቤቱ ስር ያሉ ቡድኖች ስም ዝርዝር

  1. የጤና ተቋማትና ባለሞያዎች ቁጥጥር ቡድን
  2. የጤና ተቋማት ብቃት ማረጋገጥ ቡድን
  3. የምግብ ተቋማት ብቃት ማረጋገጥ ቡድን
  4. የምግብ ተቋማት ቁጥጥር ቡድን
  5. የጤና ነክ ተቋማት ብቃት ማረጋገጥ ቡድን
  6. የጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ቡድን

 የተቋሙ ራዕይ/Vision

2017 .ም ለአዲስ አበባ ከተማ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ሳይንስን መሰረት ያደረገ የምግብ፣ መድሃኒት፣ ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ሥርዓት ተዘርግቶ ነዋሪዎቿ የቁጥጥሩ ባለቤት የሆነባትና ጤና ማህብረተሰብ የሚኖርባት ከተማ ሆናማየት፣

ተልዕኮ/Mission

  የጤና ባለሙያዎችን ሙያዊና ስነ ምግባራዊ እና የጤናና ጤና ነክ የምግብና የመድኃኒት ተቋማት ብቃት በማረጋገጥ፣ የሙያ ምዝገባ ፈቃድ በመስጠትና የኃይጅንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ እንዲሁም የአገልግሎቶችንና ግብአቶች ጥራት ደረጃቸውን ለማስጠበቅ ወቅታዊ የጤና ቁጥጥር መረጃ ለህብረተሰቡ በማቅረብ የህብረተሰቡን ጤና ማበልጸግና መጠበቅ ነው፡፡

እሴቶች/Values

  • ተጠያቂነት፣
  • ፍታዊነት
  • ታማኝነት
  • ግልጽነት፣
  • የላቀ አገልግሎት መስጠት፣
  • ለለውጥ ዝግጁነት፣
  • የህዝብ ጥቅም ማስቀደም፤
  • ጥራትን -ተቀዳሚ ተግባር ማድረግ፤ ለሙያ ስነ-ምግባር ተገዥነት፣ በእምነትና በእውቀት መምራት/መስራት/ ናቸው፡፡

 

 

 

አድራሻ

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንጻ 6ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 601

በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • የኃይጂንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት፤
  • የምግብ ተቋማት ቁጥጥር ማድረግ
  • ናሙናዎችን በመውሰድ እንዲመረመር ማድረግ እና በውጤቱ መሰረት ሙያዊ ትንታኔ መስጠት፤
  • የኃይጂንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ቁጥጥር ማድረግ፤
  • በአቤቱታና ጥቆማ የሚመጡ የአካባቢ ብክለት (የትምባሆ…ወዘተ)ና ህገወጥ የምግብ፣መጠጥና ጤና ነክ ምርቶች ላይ ችግሮችን በማጣራት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፤
  • የአገልግሎት ግዜያቸው ያለፈባቸውንና የተበላሹ የምግብ፣መጠጥና ጤናነክ ምርቶችን መወገዳቸውን ማረጋገጥ፤
  • የጤና ተቋማት ብቃት ማረጋገጥ አዲስ ፈቃድ መስጠትና እድሳት ማድረግ፣
  • የጤና ባለሙያዎች ብቃት ማረጋገጥ አዲስ ፈቃድ መስጠትና እድሳት ማድረግ፣
  • የጤናተቋማት፣የጤና ባለሙያዎችና የባህል መድኃኒት አዋቂዎች ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ፣
  • የአገልግሎት ግዜያቸው ያለፈባቸውን የተበላሹ መድኃኒትና የህክምና ግብዓት መወገዳቸውን ማረጋገጥ፣
  • አስተዳደሩ በሚቆጣጠራቸው የጤና ተቋማት አበረታች መድሀኒቶች፣የናርኮቲክ መድኃኒት፣ሳይኮትሮፒክ ንጥረነገሮች እና ፕሪከርሰር ኬሚካሎች ለህሙማን ማዘዝን ፣ማደልን ፣አጠቃቀምን ፣መመዝገብንና ሪፖርት ማድረግን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤

ከተገልጋይ የሚጠበቅበት፡- እንደየሚሰጠው አገልግሎት መስፈርትና መረጃዎችን አሟልቶ መገኘት