
Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.
ራዕይ
በአቃቂ ቃሊት ከ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ውጤታማ የትምህርት ስርዓት በማስፈን በ2020 ዓ.ም ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ የትምህርት ተቋማትንና በልማት፣ በድሞክራሲና በመልካም አስተዳደር ግንባታ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ የተሟላ ስብዕና ያለው የትምህርት ተቋማትን ማፍራት፡፡
እሴቶች
- ለትምህርት ጥራት ቅድሚያ እንሰጣለን
- በመልካም ሥነምግባር የታነፁ ዜጎችን እናፈራለን
- ፈጠራና ችግር ፈቺነትን እናበረታታለን
- ጥናትና ምርምር መለያችን ነው
- በእውቀትና በእምነት እንመራለን
- ግልፅነት
- ተጠያቂነት
- ለለውጥ ዝግጁ ነን
- የላቀ አገልግሎት እንሰጣለን
- በጋራ መስራት መገለጫችን ነው
ተልዕኮ
በአቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ት/ፅ/ቤት በት/ት ስራ ላይ በባለቤትነት በመሳተፍ ለት/ት መዋቀሩ አካላትና በት/ት መስክ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ሙያዊና ቴክንካዊ ድጋፍ በመስጠት ፣ ስራዎች፣ በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ተግባራዊ እንዲሆን መከታተልና መደገፍ፤ አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ት/ት ተቋማትን በፍትሃዊነት በማስፋፋት ደረጃውን የጠበቀና በቴኮኖሎጂ የተደገፋ ት/ት በተስማሚ ፕሮግራሞች ለህ/ሰቡ እንዲደርስ የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ፡፡
ጽ/ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702
የጽ/ቤቱ ግዴታ
- የአገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች አሟልቶ መገኘት ፤
- ስለአገልግሎቱ የተሟላ መረጃ መስጠት፤
- አገልግሎቶቹን በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት መስጠት ፤
- ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ሙያዊ የምክር አገልግሎት የመስጠት፤
- ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ለሚፈጠሩ ቅሬታዎች ቀልጣፋ ምላሽ መስጠት፤
- ለተገልጋዩ ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት፤
- በየጊዜው የህብረተሰቡ እርካታ ያለበት ደረጃን በዳሰሳ ጥናት በመለካት የህብረተሰቡን እርካታ ማወቅ
- የትምህርት ተቋማትን ከአዋኪ ነገሮች ነጻ ማድረግ
የተገልጋዮች መብት
- ስለ አገልግሎቱ የተሟላ መረጃ መግኘት
- የምክር አገልግሎት ማግኘት
- ቅሬታ የሚያቀርብበት ግልጽስርዓት፣ለሚያርቡት ቅሬታ በቃል ሆነ በጽሁፍም ፈጣን ምላሽ ማግኘት
- በየሶስት ወሩ የተቋሙ የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ መሳተፍ
- በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ሴክተሩ ተቋማት በየሚያካሂዱት የምዛና የዕውቅና ስርዓቶች ላይ በተደራጀ መልኩ መሳተፍ
- ጥራቱንና ተገቢነቱን የተረጋገጠ ትምህርት በፍትሃዊነት የማግኘት መብት
የተገልጋይ ግዴታዎች
- ትክክለኛ መረጃዎችን በማቅረብ
- የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችን መሟላት ማቅረብ
- የአገልሎት ሰጪ ተቋማትን ህግና ስርዓትን ማክበር
- በክትትልና ሱፐርቪዝን የሚሰጡ የማሻሻያ ግብዓቶችን ተግባራዊ ማድረግ
- ወላጆችን ህብረተሰቡ የትምህርት ስርዓቱን በግብዓትና በመማር ማስተማር ሂደት እና ውጤት ማሻሻል ድርሻውን መወጣት
- የትምህርት ተቋማትን ከሰው ሰራሽ አዋኪ ነገሮች መጠበቅ
- ወላጆችና ህበረተሰቡ ተማሪዎችን መምከር
- ተገላጋዩ የሚጠበቅበትን ዲፕሊን ማክበር
የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት
- ቅሬታ ያጋጠመው ዜጋ ቅሬታውን በቀጥታ አገልግሎት ለሰጠ በቃል፣በጽሁፍ፣በስልክ መግለጽ ይችላል፤
- ቅሬታ የቀረበበት ፈጻሚም የቀረበለትን ቅሬታ አጣርቶ ወዲያውኑ ለቅሬታ አቅራቢው ተገልጋይ ተገቢውን ምላሽ መስጠት አለበት፤
- በተሰጠው ምላሽ ያልረካ ተገልጋይ ቀጥሎ ላለው የቅርብ ሃላፊ አገልግሎት ላላገኘበት የስራ ሂደት /ቅሬታው እንዲፈታለት ማቅረብ ይችላል፤
- ደረጃውን ጠብቆ የቀረበለት የቡድን/ስራ ሂደቱ ሃላፊ/አገልግሎት ላላገኘበት የስራ ሂደት /ቅሬታውን አጣርቶ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠት አለበት፤
- በተሰጠው ምላሽ ያልረካ ተገልጋይ ለተቋሙ የቅሬታና አቤቱታ ሰሚ አካል ወዲያውኑ ቅሬታውን ያቀርባል፤
- የቅሬታና አቤቱታ ሰሚ አካል የቀረበለትን አቤቱታ አጣርቶ ምላሽ መስጠት በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ በ5 ቀናት ውስጥ ምላሽ ይሰጣል፤
- የቅሬታና አቤቱታ ሰሚ አካል የቀረበለትን አቤቱታ በማጣራት የበላይ አመራር ውሳኔ የሚያስፈልገው ከሆነ ከውሳኔ ሃሳብ ጋር ያቀርባል፤
- የመ/ቤቱ የበላይ አመራር ከሚቀርቡለት የውሳኔ ሃሳቦች ላይ በመነሳት በሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ ምላሽ ይሰጣል፤
- በዚህም ውሳኔ ተገልጋዩ ዜጋ ካልረካ በየደረጃው /በክፍለከተማና በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር/ለሚገኘው የህዝብና ቅሬታ ና አቤቱታ ሰሚ ዋና የስራ ሂደት ቅሬታውን ያቀርባል፡፡
- በዚህም ውሳኔ ተገልጋዩ ዜጋ ካልረካ ለሚመለከተው ፍርድ ቤት፣ጸረ ሙስና ኮሚሽን፣ለህዝብ እንባጠባቂ ፣ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መብት ማቅረብ ይችላል፡፡