የመንግስት ንብረት አስተዳደር ፅ/ቤት

የስራ ሂደቶች

  1. የመንግት ንብረት ክትትል ና ድጋፍ ቡድን አስተባባሪ
  2. የመንግት ንብረት ስራ አመራር አስተባባሪ
  3. የመንግስት ንብረት ኦዲት ቡድን
  4. የመንግስት ንብረት ህንጻ ጥገና እና ዕድሳት ቡድን
  5. የህንጻ መሰረተ ልማት መገልገያ መሳሪያ እና ዕድሳት ቡድን
  6. የፋሲሊቲ አገልግሎት ቡድን
  7. የምድረ -ግቢ ማስዋብና ደህነት ቡድን

ራዕይ

በ2017ዓ.ም ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ምቹ፣ ቀልጣፋ ውጤታማ አገልግሎት የሚሰጥባቸው የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ህንጻዎች ለምተውና ዘመናዊ የንብረት አያያዝ ስርዓት ተዘርግቶ ማየት፡፡

ተልዕኮ

በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች ህንፃና ምድረ ግቢ በወጥ ዲዛይንና ወጪ በሚቆጥብ መልኩ እንዲለማ በማድረግ፣ የህንፃ የውስጥ አደረጃጀትና የንብረት አስተዳደር ስታንዳርድ በማዘጋጀትና በማስተግበር፣ ፍታሃዊ የሀብት ድልድል እንዲኖር በማስቻል፣ ደረጃውን የጠበቃ የጥገና፣ እድሳት የንብረት አወጋገድ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት፣ የህንፃና ንብረት  ምዝገባ ስርዓቱን በማዘመንና የተማላ መረጃ እንዲያዝ በማድረግ እንዲሁም የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ በማደረግ  ውጤታማ የህብት አስተዳደር ማስፈን ነው፡፡

እሴቶች

  • ውጤታማ የሃብት አጠቃቀምን እናሳድጋለን፤
  • ለውጤታማነት በቡድን እንሰራለን፤
  • ውብና ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር እንሰራለን፤
  • የዘመነ የመረጃ አያያዝ ስርዓት እንዲኖር እንተጋለን፤
  • ጥራት ላለው ወቅታዊ መረጃ ተደራሽነት እንሰራለን፤
  • አዳዲስ ሀሳቦችን እናፈልቃለን፤
  • ተጠያቂነትን እናሰፍናለን
  • የአገልጋይነት መንፈስን ተላብሰን እንሰራለን፣
  • ለመማርና ለለውጥ ምንጊዜም ዝግጁ ነን፤

ለአዳራሽ አገልግሎት ጥያቄ ሲመጣ ተገልጋይ ሟሟላት ያለበት

  1. ለሚጠይቀው አዳራሽ በደብዳቤ መጠየቅ
  2. በአዳራሹ የሚገኘው የሰው ብዛት
  3. .ለስንት ቀን እንደሚፈልጉ
  4. በአዳራሹ የሚከናወኑ ኩነቶችን መግለጽ
  5. በጠያቀው ጽ/ቤት ጋላፊ ፊርማ መጠየቅ ደብዳቤው ከ3ቀን በፊት ማስገባት .

በቢሮ ውስጥ የመብራትና የውሃ ችግር ተፈጥሮ ለሚጠየቅ አገልግሎት

    1.በደብዳቤ ወይም በቃል የተቋረጠውን የመብራት ፣የውሃ አገልግሎት የትኛውም እንደሆነ ማሳወቅ ፡፡

  1. ብልሽቱ (ጉዳቱ)የደረሰበትን በማን እንደሆነ ማሳወቅ፡፡
  2. የሚጠገነው የተበላሻው መብራት ወይም ውሃ መሆኑን መግለጽ፡፡

የሕጻናት ማቆያ ተቋም (ዳይኬር) ለመጠየቅ የሚቀርብ አገልግሎት ጥያቄ

  1. ወደ የሕጻናት ማቆያ (ዳይኬር) የሚያመጡት ህጻን ዕድሜያቸው ከ6ወር አስከ 4 ዓመት
  2. ወደ ህጻናት ማቆያ ተቋም ህጻናት ሲመጡ የክትባት ካርድ ማምጣት
  3. ወደ ህጻናት ማቆያ ተቋም ህጻናት ሲያመጡ የህጻናት ቤተሰብ ስልክ ወይም ሙሉ መረጃ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡

አድራሻ

በአቃቂ ቃሊ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 7ተኛ ፎቅ በስተቀኝ    በኩል ቢሮ ቁጥር 705.