‹‹እንስራ ሌማታችን ሞልቶ ይትረፍረፍ››

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ አንድ አስተዳደር የሌማት ትሩፋት መርሀ-ግብር በይፋ አስጀመረ፡፡

ህዳር 22/2015 ዓ/ም (አቃቂ ቃሊቲ)

በመርሐ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ እና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ፣ የክ/ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መዝገበ ይስማው፣ የክ/ከተማው ም/ስራ አስፈጻሚ እና የስራ እድል ፈጠራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር፣ የክብር እንግዶች እና የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በኑሮ ውድነት ያለውን ፈተና መቋቋም የሚቻለው የህብረተሰቡን የገቢ አቅም በማጠናከር እንዲሁም የስራ እድል በመፍጠር ምርትና ምርታማነትን በገጠር ብቻ ሳይሆን በከተማም መተግበር ስንችል ነው ብለዋል፡፡

አክለውም ህብረተሰባችን ውስጥ ትልቅ ድህነት አለ ነገር ግን በየቦታው የሚታዩ ጾማቸውን የሚያድሩ መሬቶች አሉ ይህንን ማስታረቅ እንደሚገባ፤ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚቻለው ባለን ነገር ማልማት ስንችል ነውና ማህበረሰቡም ይህንን በመረዳት የዚህ መርሀ-ግብር ተሳታፊ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደስታ ፊሊጶስ በበኩላቸው በሌማት ትሩፋት በቂ እና አመርቂ የሆኑ ምርቶችን አቅርበን የተትረፈረፈ ማዕድ በፍቅር የምንቆርስበት፤ በደማችን አጽንተን ያቆየነውን ሉአላዊነታችንን በላባችን ዳግም የምናረጋግጥበትና የምናጸናበት ትልቅ ንቅናቄ ነው በማለት ሁሉም ለዚህ ንቅናቄ መሳካት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክትና ርብርብ እንዲያደርግ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ማእከል ለወረዳው በምርምር የበለጸጉ 10 ሺ ዶሮዎችን በዘርፉ ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በክቡር ም/ከንቲባው በነፍስ ወከፍ የሚጠቀሟቸው ዶሮዎችን የማረካከብ መርሀ ግብር የተከናውኗል።

በተያያዘም በእለቱ ከሌማት ትሩፋት ጎን ለጎን ከሚከናወኑ የ90 ቀናት እቅድ ተግባራት መካከል የአቅመ ደካሞችን የቤት እድሳት ለማስጀመር ከበለሀብቶች ጋር ርክክብ ተደርጓል።

 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተናገሩ ፦

 

    • አሁንም ማንኛውም ችግር ቢያጋጥም በፍጥነት እናርማለን፤ በኦዲት ጭምር እናረጋግጣለን።

    • በ20/80 93,352 በ40/60 54,540 በድምሩ 146,892 ከባንክ በተገኘው መረጃ መሰረት እንዲጣራ ተደርጎ ወደ ሲስተሙ ገብቷል። በዚህም ብቁ እና ንቁ ተብለው ለዕጣው ተዘጋጅተዋል።

(ከንቲባዋ በንግግራቸው በድምር ሲሉ የገለፁት ቁጥር (93,352 + 54,540) 146,892 አጠቃላይ ድምሩ የሚመጣው 147,892 ነው ፤ ይህ ትላንትም በከተማው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ተገልጾ የነበር ሲሆን ለምን ይህ ሊሆን እንደቻለ የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ እንጥራለን።)

 

    • በ1997 ተመዝጋቢ የነበሩ ባለ 3 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ባለፈው ከዕጣ አወጣጡ ውጭ ተደርገው ነበር ፤ በዚህም በቀረበው ቅሬታ ከ2005 ቆጣቢዎች ጋር ዛሬ ለዕጣ ብቁ እንዲሆኑ ተደርገዋል።

    • ዛሬ ለዕጣ የተዘጋጁት 25,791 ቤቶች ከ1997 ብቁ እና ንቁ ተመዝጋቢዎችን ሙሉ በሙሉ በመያዝ ለዕጣው መውጣት ዝግጅቱ የተደረጉ ናቸው።

    • ከዚህ በኃላ በ1997 የሚጠራ ብቁ እና ንቁ ተብለው የሚጠሩ ዕጣ የሚወጣላቸው የተለየ ሁኔታ ሳያስፈልግ ሙሉ ተመዝጋቢዎች ዛሬ ይስተናገዳሉ።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከማኅበረሰቡ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄደ

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት “በደም የከበረ በላብ የታሠረ” በሚል መሪ ቃል በክፍለ-ከተማው ከሚገኙ ከተለያየ ማህበረሰባዊ መሠረት ከተወጣጡ ነዋሪዎች ጋር ተወያይቷል።
በውይይቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ እና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መዝገበ ይስማው እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መዝገበ ይስማው ሲሆኑ ሰነዱም በሶስት አጀንዳዎች ላይ ማለትም በለውጡ የመጡ ለውጦች፣ የሌማት ቱሩፋቶች እና የሰላም ስምምነቱ አንድምታዎች ዙሪያ የተዘጋጁ ሲሆን በዝርዝር ለተሳታፊዎች ቀርቧል።
በውይይቱም በመስዋዕትነት የቆመን ሃገር በላብ የሚያፀኑ ዋነኛ ማጠንጠኛ ጉዳዬችን አሳይተዋል በዚህም በማይናወጥ ኢኮኖሚ፣ በአዳጊ ፖለቲካ፣ በሚያስተሳስር ማህበራዊ ገመድ እና ጠንካራ ዲፕሎማሲ ላይ መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።
መንግስት ባመቻቸው አቅጣጫ አሁን ላይ ወቅታዊ አጀንዳ በሆነው “የሌማት ትሩፋት ” ስራዎችን አጠናክሮ በመስራት የከርሰ ምድር እና የገፀ ምድር ውሃን በመጠቀም እንደ ክፍለ ከተማ 35,403 (ሰላሳ አምስት ሺ አራት መቶ ሶስት) ሰዎችን በማሳተፍ በጦር ሜዳ ደማችንን በኢኮኖሚ ግንባር ላባችንን አፍሰን በርካታ ድሎች ማስመዝገብ ችለናል ብለዋል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን ጦርነት በሶስት ዙሮች ከፍተኛ የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ተስተናግደዋል፤ አሜሪካ በህወሃት ፈረስ ላይ መጋለቡን ለማስቆም የአፍሪካዊያን ችግር በአፍሪካዊያን መፍትሄ እንዲያገኝ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱም ተጠቅሷል።
መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው በህዝባችን ደጀንነት፣ በመከላከያችን ጀግንነት እና በመንግስታችን ብስለት አሁን ላይ የትግራይ እናቶች እና ጦርነቱ ሲካሄድባቸው የነበሩ አካባቢዎች የሰላም አየር እየተነፈሱ ነው ብለዋል።
በተያያዘም አሁን ላይ በትኩረት በተያዘው የሌማት ቱርፋት ዘመቻ ላይ አመራሩ እና ህዝቡ በቁርጠኝነት በመስራት በጦርነቱ የታየውን አሸናፊነት በምግብ ራሳችንን በመቻል ለልመና የሚዘረጉ እጆች ለስራ እንዲነሱ በማድረግ በእያንዳንዱ ቤት የሚጎረስ ዳቦ ማስገኝት ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ በበኩላቸው እኛ ኢትዮጵያዊያን የዕምቅ ሀብት ባለቤት ሆነን በድህነት መታወቅ የለብንም በዕለተ ተዕለት የምንመገበው ምግብ ላይ አስፈላጊ እና ጠቃሚ የሆኑ ምግቦችን በማምረት እንደ ብርቅ የንቅጦት ተደርገው የሚቆጠሩ ምግቦችን ማግኝት እንችላለን ብለዋል።
ተወያዮችም የቀረበው ሰነድ ይበል የሚያስብል መሆኑን በመግለጽ ፣የተጀመረውን ሰላም በማስጠበቅ የሌማት ትሩፋቱን ተግባራዊ ለማድረግ ከአመራሩ ጋር በጋራ በመሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል፤ በተጨማሪም አንዳንድ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን እና ሀሳብ አስተያየቶችን አንስተዋል።
በመጨረሻም ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረክ መሪዎቹ ተገቢው ምላሽ ተሰጥቶባቸው መድረኩ ድምዳሜ አግኝቷል።