የመሬት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

በጽ/ቤቱ ስር ያሉ ስራ ሂደቶች

  1. የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
  2. የካዳስተር አገልግት ቡድን
  3. የመብት አገልግሎት ቡድን
  4. የተረጋገጠ መብት ምዝገባ ቡድን
  5. የማህደርና ዶክመንቴሽን ደህንነትና አስተዳደር ቡድን
  6. የመረጃ ስርጭት ቡድን
  7. የአድራሻ ስርአት ቡድን
  8. የቅሬታና አቤቱታ ኦዲት ቡድን
  9. የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን

ራዕይ

በ2022 ለከተማችን የመሬት አስተዳደር ስርዓት ልህቀት መሰረት የሆነ የህጋዊ ካዳስተርና ዘመናዊ የተቀናጀ የመሬትና መሬት ነክ መረጃ ማኔጅመንት ስርዓት እውን ሆኖ ማየት፤

ተልዕኮ

በአዲስ አበባ ከተማ ወሰን ውስጥ የሚገኙ የመሬት ይዞታዎችን ሙሉ በሙሉ አረጋግጦ በመመዝገብ አስተማማኝና ዘመናዊ የህጋዊ ካዳስተር ስርዓት በመገንባት፤ የተቀናጀ የመሬትና መሬት ነክ መረጃ ማኔጅመንትና ዘመናዊ የአድራሻ ሥርዓት በመዘርጋት ቀልጣፋና ውጤታማ የመሬት ምዝገባና መረጃ አገልግሎቶች በመስጠት የከተማችንን የዘመናዊ መሬት አስተዳደር ሥርዓት ሽግግርና ልህቀት ማረጋገጥ፡፡

ዕሴቶች/Values)

  • አገልጋይነት
  • መረጃ ቀዳሚ ኃብታችን
  • ታማኝነት
  • ተጠያቂነት
  • በዕውቀትና በክህሎት መምራት
  • ግልጽነትና አሳታፊነት
  • ለለውጥ ዝግጁ መሆን
  • የቡድን ሥራ ለስኬታማነት

አድራሻችን

  • የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ከጀርባ G+3 ወለል ያለው

ተቁ

የምንሰጣቸው የአገልግሎት አይነቶች

ከተገልጋይ መሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታዎች

1

   በተረጋገጠ ይዞታ ምዝገባ/ አዲስ የይዞታ ማረጋገጫ ምዝገባ

በተጨማሪ

      የይዞታ ማረጋገጫ  ውጤት

      በይዞታ አስተዳደር የተሰጠ የይዞታ ካርታ

      ለይዞታ ማረጋገጥ ያመለከቱበት ከሆነ ቅፅ 04

      የሊዝ ይዞታ ከሆነ የዘመኑን የሊዝ የተከፈለበት ማስረጃ

 

2

   የባንክ ዋስትና ምዝገባ/ሰረዝ አገልግሎት

 በተጨማሪ

      የንብረት መያዣ እንዲመአገብለት ወይም እንዲሰረዝለት ከሙፈልገው ህጋዊ አካ ደብዳቤ ማቅረብ

 

3

   የፍርድ ቤት እግድን መመዝገብ/ መሰረዝ

      የዕግድ ማንሻ/መመዝገቢያ ደብዳቤ ማቅረብ

 

4

   የስመ-ንብረት ዝውውር አገልግሎት መስጠት

      በሽያጭ ወይም በስጦታ ሲሆን በተጨማሪ

v  በህግ ስልጣን በተሰው አካል የፀደቀ ውል

v  የሊዝ ውል

 

      በሊዝ የተያዘ ሲሆን በተጨማሪ

v  በውሉ መሰረት መክፈል ያለባቸው ክፍያዎች ከፍሎ ማጠናቀቅ ወይንም የሚዛወርለት ወገን ክፍያውን ለመፈፀም እንዲሁም አስተላላፊው ቀደም ሲል በገባው ውል ላይ  የተጠቀሙበትን ግዴታዎች ገዥ ሙሉ በሙሉ በመቀበል ውል የገባበትን ከሚመለከተው አካል ማቅረብ

v  በቦታው ላይ የተደረገው ከ50 በመቶ ያነሰ ከሆነ የተሸሻለ የሊዝ ውል

 

 

      በባንክ ሐራጅ የተሸጠ ሲሆን በተጨማሪ

v  ከባንክ አሸናፊው ያሸነፈበትን ዋጋ የሚገልፅ ደበዳቤ

v  የሊዝ ከሆነ በሐራጅ የገዛው አካል በስሙ የሊዝ ውል ተዋውሎ ሲቀርብ

v  ነባር ይዞታ ከሆነ አዲስ የሊዝ ውል

 

      በፍርድ አፈፃፀም የተሸጠ ሲሆን በተጨማሪ

v  የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ኦርጅናል

v  በሊዝ የተያዘ ይዞታ ከሆነ ሻጩ  የገባውን የሊዝ ግዴታዎች ገዥ  ሙሉ በሙሉ የሚቀበል መሆኑን እንዲሁም ዕዳ ያለበት ከሆነ  ዕዳውን ለመክፈል ስምምነት ማቅረብ

v  ነባር ይዞታ ከሆነ አዲስ የሊዝ ውል

 

      በፕራይቪታይዜሽን ኤጀንሲ የተላለፈ ሲሆን በተጨማሪ

v  ከኤጀንሲ ያሸነፉበትን ዋጋና የሽያጭ ውል የሚገልፅ ሰነድ ማቅረብ

 

      የመኖሪያ ቤት ህ/ስራ ማህበራት አባላት መተካካት ሲሆን ወይም ግንባታቸው ያልተጠናቀቀ ሲሆን በተጨማሪ

v  ከማህበራት ማደራጅ የማህበሩና መተካካት ሂደቱ ህጋዊነት የተረጋገጠበት ደብዳቤ ማቅረብ

 

      የጋራ ህንፃ /ኮንዶሚኒም ሲሆን በተጨማሪ

v  የባንክ እዳ ተከፍሎ መጠናቀቁን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ

v  የመኖሪያ ቤትከሆነ ከ5 ዓመት የግዜ ገደብ ማብቃቱን የሚያስረዳ መረጃ ማቅረብ

 

      በውርስ የተገኘ ይዞታ ሲሆን በተጨማሪ

v  የውርስ ባለመብትን የሚያረጋግጥ የፍ/ቤት ውሳኔ በፍ/ቤት የጸደቀ የውርስ አጣሪ ሪፖርት

v  የድርሻ መጠን ማስረጃና ስምምነት ማቅረብ (ካልተከፋፈሉም በጋራ የሚመዘገብ ይሆነል)

v  የሊዝ  ይዞታ ከሆነ ያልተከፈለ የሊዝ ካለ ክፍያ መፈጸሙን የሚያስረዳ መረጃ ወይም ለመክፈል የገቡት ስምምነት ማቅረብ

 

5

   ለጠፋ(ለተበላሸ) ሰርተፍኬት ምትክ መስጠት

በተጨማሪ

Ø  ማስረጃው ለመጥፋቱ በህጋዊ አካላት የተሰጠ ሰርተፍኬት ጠፍቶ ከሆነብቻ

Ø  የተበላሽ ከሆነ የተበላሸው የይዞታ ማረጋገጫ  ማስረጃ ሰርተፍኬት

Ø  የግዴታ ውል መግባት

Ø   

6

   የወሰን ምልክት ማመልከት እና ለወሰን ክርክሮች ማስረጃ መስጠት

በተጨማሪ

Ø  ሁለት ጉርድ ፎቶ (3*4) ከአንድ በላይ ባለይዞታዎች ከሆነ የሁሉም ባላይዞታዎች

7

 

   የወሰን ነጥብ መቀየር

 

         የወሰን ነጥብ ለመቀየር በተጨማሪ

 

Ø  የድንበር  ለውጡን ያስከተለው ህጋዊ  ማስረጃ ማቅረብ

 

8

 

   ይዞታ መክፈል አገልግሎት መስጠት

 

በተጨማሪ

v  የሊዝ ይዞታ ከሆነ ግዜው ያላለፈበት የሊዝ ውል

 

9

 

      ይዞታ መቀላቀል አገልግሎት መስጠት

 

ይዞታ ሲቀላቀል በተጨማሪ

Ø  የሊዝ ይዞታ ከሆነ የተሻሻለ የሊዝ ውል ኦርጅናል እና

Ø  የፕላን አስተያየት ከሚመለከተው አካል ማቅረብ

 

10

 

   የሪል እስቴት& የኮንዶሚኒየም  እና የማህበራት(የጋራ ህንፃ) የተናጥል ሰርተፍኬት መስጠት

የተናጥል ሰርተፍኬት ሲሆን በተጨማሪ

Ø  የሪል ስቴት ከሆነ አግባባ ባለው አካል የፀደቀ የግንባታ ፍቃድ/ዲዛየን እና ግንባታው ስለመጠናቀቁ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ

11

   የምዝገባ ማሻሻያ /የመረጃ ወቅታዊ ማድረግ አገልግሎት መስጠት

በተጨማሪ

Ø  ወቅታዊ የሚደርገውን መረጃ የሚቀይር ህጋዊ ማስረጃ ዋናውን ከሚመለከተው አካል ማቅረብ

Ø   

12

   የቦታ መጠቀሚያ ኪራይ እና የህንፃ/ቤት ግብር ተመን አገልግሎት መስጠት

በተጨማሪ

Ø  አስፈላጊ ሲሆን ቤቱ የተገነባበት ፕላን ማቅረብ

 

 

13

 

 

   የንብረት ግምት አገልግሎት መስጠት

 

የሊዝ ይዞታ ከሆነ በተጨማሪ

 

Ø  የሊዝ ውል ማሻሻያ ማቅረብ

Ø  አስፈላጊ ሲሆን ቤቱ የተገነባበት ፕላን ማቅረብ

 

14

 

   የይዞታ አገልግሎት ለውጥ መመዝገብ

 

የሊዝ ይዞታ ከሆነ በተጨማሪ

 

  • የሊዝ ውል ማሻሻያ ማቅረብ

 

15

 

   ለፍትህ ተቋማት ምላሽ መስጠት

በተጨማሪ

Ø  ከፍትህ ተቋማት የተፃፈ ዋናው (ኦርጅናል) ደብዳቤ ማቅረብ

16

 

   መሬት ነክ መረጃዎች ስርጭት መስጠት

Ø  የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት (ማመልከቻ)

Ø  የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ&ፓስፖርት&መንጃ ፍቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ

Ø  ወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ

Ø  የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ኮፒ

Ø  የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም

17

 

   ይካተትልኝ አገልግሎት መረጃ መስጠት

18

 

   ህጋዊ የካዳስተር ቅጂ አገልግሎት መስጠት