
በጽ/ቤቱ ስር 5 የሥራ ክፍሎች ይገኛሉ
- የጽ/ቤት ሀላፊ
- የኦኘሬሽክ ክፍል ዳይሬክተር
- የህዝብ ጭነት ስምሪት ቁጥጥር ድልድል ቡድን መሪ
- የመሰረተ ልማት ክትትል ቁጥጥር ቡድን መሪ
- የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን መሪ
ራዕይ
ተደራሽ ፣ ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ ፣ ምቹ፣ የተጠበቀ እና ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የሆነ አቅምን ያገናዘበ የብዙሀንና የጭነት ትራንስፖርት ለህብረተሰቡ ማቅረብ
ተልዕኮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንፖርት ቢሮ የህዝብና ጭነት ትራስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የሚሰሩ ማህበራትና ተቋማትን ፣ ግለሰቦችን በማደራጀት የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶችን በማልማትና በማስተዳደር ጥናቶችን በማካኤድ ስምሪት በመስጠት በመቆጣጠር እና መረጃን ተደራሽ በማድረግ የተገልጋይ ህብረተሰብ የተቀናጀ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ፡፡
እሴት
- ለለውጥ ዝግጁነት
- ፍትሀዊነት
- ተጠያቂነት
- ግልፅነትና
- የላቀ አገልግሎት
የሚሰጡ አገልግሎቶች
- አዲስ ታፔላ መስጠት ማደስ
- የሀይገርና ታክሲ ስምሪት ማፅደቅ መከታተል
- የመጠበቂያ መጠለያዎችን የመቆጣጠር የመከታተል ስራ
- ተራ አስከባሪዎችን የመቆጣጠር የመከታተል ስራ
በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደረጃ የሚሰጥ አገልግሎት
ተ.ቁ | የሚሰጡ አገልግሎቶች ዓይነት | አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ | የአገልግሎት ስታንዳርድ/ደረጃ | የሚሰጥበት ሁኔታ | ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታዎች | |
ጊዜ /በሰዓት/ | ጥራት /በ%/ | |||||
1 | የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ድልድል አገልግሎት መስጠት፣ | |||||
1.1 | የታክሲ ማህበራት የስምሪት ድልድል ማጽደቅ | የትራንስፖርት ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት | 0፡16 | 100 | በአካል | § የስምሪት መስመር ሽክርክሪት በተቀመጠው አሰራር መሰረት አዘጋጅቶ ማቅረብ፤ |
1.2 | የድጋፍ ሰጭ የስምሪት መስመር አገልግሎት መስጠት | 0፡30 | 100 | በአካል | § የተዘጋጀለትን ፎርም ሞልቶ ማቅረብ፤ § አዲሰ ከሆነ ሊብሬና መታወቂያ፤ ባለቤት ካለሆነ ህጋዊ ውክልና ነባር ከሆነ የቀድሞ የታፔላ መመለስ፤ § የአገልግሎት ክፍያ 590 ብር መፈጸም | |
1.3 | የስምሪት መስመር አገልግሎት ውል ማቋረጥ | 0:30 | 100 | በአካል | § በባለበቱ ወይም ህጋዊ ውክልና ዯለው አካል በአካል መቅረብ አለበት § የታደሰ መታወቂያ § የውስጥ እና የውጭ ታፔላ ይዞ መገኘት አለበት | |
1.4 | የማህበራት የተማሪዎች ሰርቪስ አገልግሎት ጥያቄ ማስተናገድ | 0፡20 | 100 | በአካል | § የተሽከርካሪዎችን ድልድል በተቀመጠው አሰራር መሰረት አዘጋጅቶ ማቅረብ፤ | |
2. | የሕዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ክትተልና ቁጥጥር ማካሄድ | |||||
2.1 | የአሽከርካሪዎች ቅጣት ክፍያ፤ | የትራንስፖርት ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት | 0፡10 | 100 | በአካል | § በትራንስፖርት ስምሪት ቁጥጥር ሠራተኛ የተቆረጠ የቅጣት ማዘዣ /ደረሰኝ/፤ |
3 | ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎቶች የኦፐሬሽን ስርዓትና መቆጣጠር | |||||
3.1 | የአሽከርካሪዎች ቅጣት ክፍያ፤ | የትራንስፖርት ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት | 0፡10 | 100 | በአካል | § በትራንስፖርት ስምሪት ቁጥጥር ሠራተኛ የተቆረጠ የቅጣት ማዘዣ /ደረሰኝ/፤ |
- ከተገልጋይ የሚጠበቅ
አዲስ የኮድ 3 እና ቅጥቅይ ተሽከርካሪዎች ታፔላ ለመውሰድ ሲመጡ የሚያስፈልጉ
- ኦርጅናል ሊብሬ አድራሻው አቃቂ ቃሊቲ መሆን ይኖርበታል
- ሶስተኛ ወገን
- ቦሎ
- ንግድ ፈቃድ
- የቀበሌ መታወቂያ
- ህጋዊ ውክልና ወይም ባለቤት መሆን ይኖርበታል
አድራሻችን፡-ማሰልጠኛ ቅጥር ግቢ ውስጥ በር ሁለት