
ራዕይ፤
አዲስ አበባ ከተማ/አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ/ በ2022 ዓ.ም ከብክለት የጸዳችና በአረንጓዴ ልማት የበለፀገች ተመራጭ ከሆኑ የአፍሪካ ከተሞች አንዷ ሆና ማየት፡፡ (ከ/ከተማችን በ2022 ዓ.ም ከብክለት የጸዳችና በአረንጓዴ ልማት የበለፀገች ተመራጭ ከሆኑ የ11 ክ/ከተሞች አንዷ ሆና ማየት) ፡፡
ተልዕኮ፤
አዲስ አበባ ከተማን/አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ/ በቴክኖሎጂና በአካባቢ ህጎች የታገዘ የብክለት ክትትልና ቁጥጥር ስርአት በመዘርጋት፣ የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ብልጽግናን ከአካባቢ ደህንነት ጋር በማጣጣም፤ ለነዋሪዎቿ ተደራሽ የሆነ የነፍስ ወከፍ የአረንጓዴ ሽፋንን በማሳደግ፤ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ፤ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ልማት ያላት ከተማ መፍጠር ነው፡፡ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ
በጽ/ቤቱ የሚሰጥ አገልግሎት
- በክ/ከተማው የሚገኙ ስነ-ምህዳሮችንና ብዝሃ ሕይወት በማጎልበት፣ በመጠበቅና እንዲሻሻሉ በማድረግ ሁለንተናዊ ጠቀሜታ እንዲሰጡ ማድረግ፤
- የደንና የአረንጓዴ ቦታዎች ሀብት ልየታ ምዝገባና ማኔጅመንት ስርዓት እንዲዘረጋ በማድረግ የደን ሃብቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና አካባቢዊያዊ ጥቅም እንዲሰጥ ማድረግና ከብክነት መከላከል(100%)
- በክ/ከተማው የሚገኙ ስነ-ምህዳሮችንና ብዝሃ ሕይወት በማጎልበት፣ በመጠበቅና እንዲሻሻሉ በማድረግ ሁለንተናዊ ጠቀሜታ እንዲሰጡ ማድረግ (100%)
- የደንና የአረንጓዴ ቦታዎች ሀብት ልየታ ምዝገባና ማኔጅመንት ስርዓት እንዲዘረጋ በማድረግ የደን ሃብቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና አካባቢዊያዊ ጥቅም እንዲሰጥ ማድረግና ከብክነት መከላከል (100%)
- በማዕድን ማምረት የተጎዳውን ቦታ መልሶ መልማቱን መከታተል፤ ህጋዊ የማዕድን ማምረት ስራ እንዲኖር መቆጣጠርና የዕርምት እርምጃ መውሰድ (100%)
- የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስልትን ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከአገረ አቀፍ ስልት ጋር በማጣጣምና ሴክተር መስሪያቤቶች በእቅድ አካትተዉ እንዲተገብሩ ከትትልና ድጋፍ በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖዎችን ለመቋቋምና ለመከላከል ብሎም ዘላቂ ልማትና እድገትን ማረጋገጥ፡፡
- በጥናት ላይ የተመሠረተ የኮንስትራክሽን ማዕድን ፍላጎት በማሟላት ሥራው ሲጠናቀቅ በማስተር ፕላኑና በስታንዳርዱ መሠረት ደረጃውን የጠበቀ የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች ጥራት እንዲኖር ማድረግ፤
ከተገልጋይ መሟላት የሚገባቸው መረጃዎችና ዋናዋና ተግባራት፤
- ብክለት ቁጥጥርና ክትትል ስራ ጋር በተየያዘ ተግባሩን ትኩረት በመስጠት አስፈላጊውን ሁሉ አገልግሎት በማመልከቻና የተለያዩ መሟላት ያለባቸውን ሰነዶች ቀድሞ በማሟላት አገልግሎት ማግኘት ይችላል፤
- የአየር ንብረት ለዉጥ እቅድ ትግበራ ማካተት /ሜይንስትሪሚንግ/ ጋር በጠያያዘ የኢነርጅና አየርንበረት ጋራ ተያያዘ ማንኛውንም ተግባር ትኩረት በመስጠት አግልግሎት ማግኘት፤
- የኮንስትራክሽን ማዕድን ፈቃድና ይሁንታ አገልግሎትን ማግኘት፤/በማመልከቻና አባሪ መረጃዎችን በማሟላት አገልግሎት ማግኘት ይቻላል፤
- የብዝሃሕይዎትና የአረንጓዴ ልማት እንዲሁም ከስነ-ምህዳር ጋር፤
በተየያዘ ሊያገኝ የሚፈልገውን ማኛውም አገልግልት የጽ/ቤቱን ስልጣንና ሃለፊነት በመገንዘብ በማመልከቻና በአካል በመቅረብ ማንኛውንም አይነት አገልግሎት መፈጸም ይኖርበታል፡፡