
በጽ/ቤቱ ስሩ ያሉ ስራ ሂደት
- የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ጽ/ቤት የኩነት አገልግሎት ቡድን
- የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ጽ/ቤት የነዋሪዎች አገልግሎት ቡድን
ራዕይ
- በ2017 ዓ.ም የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና የነዋሪዎች ምዝገባ አገልግሎቶችን ዘመናዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ስርዓትን በመዘርጋት ለህግ፣ ለአስተዳደር እና ለስታትስቲክስ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ማየት፡፡
እሴቶች
- ተጠያቂነት
- ግልጽነት
- የላቀ አገልግሎት መስጠት
- ለለውጥ ዝግጁ መሆን
- በእውቀትና በእምነት መመራት
- ኪራይ ሰብሳቢነትን በጽናት መታገል
- መልካም የሥራ ግኑኙነት በመፍጠር ለጋራ ዓላማ መቆም
ተልዕኮ
- ስለወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ያለው ሀገራዊ ፋይዳ ነዋሪው የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጣ ግንዛቤውን በማሳደግ፤ የወሳኝ ኩነት እና የነዋሪዎች ምዝገባ መረጃ እና ማስረጃ በመልካም ፈቃደኝነት እና ተነሳሽነት የማስመዝገብ ባህሉን ማሳደግ፤
- ዘመናዊ የአሰራር ስርዓትን በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የኩነት መረጃ በብቃትና በጥራት በመሰብሰብ ለፖሊሲ ቀረፃ፣ ለአገራዊ ስትራቴጂ አቅጣጫ፣ ለዕቅድ ዝግጅት እና ለማህበራዊ አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ፤
- አዳዲስ የአሰራር ስልት በመቀየስ በክ/ከተማ ደረጃ ወጥ እና ዘመናዊ የመረጃ ቅብብሎሽ እና አቅርቦት ስርዓት መገንባት እና ማደራጀት ነው
- የምዝገባ ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ ጥናት እና ምርምር ማድረግ፤ ስልጠና እና የግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባራን በማከናወን የአሰራር ስርዓቱን የተሻለ እንዲሆን ማድረግ ነው፤
- የከተማ ነዋሪዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመመዝገብ ዲጅታል የነዋሪነት መታወቂያ እና ሌሎች የነዋሪነት አገልግሎቶችን ለመስጠት ዘመናዊ የሆነ የምዝገባ ስርዓትን በመዘርጋት ተዓማኒ፣ ፍትሃዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የነዋሪዎች አገልግሎቶችን መስጠት፡፡
በጽ/ቤታችን የምንሰጠዉ አገልግሎት
1. የኩነት አገልግሎት
ተ.ቁ | የአገልግሎት ዓይነት | የሚወስደዉ ጊዜ | አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ |
1. | ልደት
| 19 ደቂቃ | በወረዳዎች |
2. | ጋብቻ | 38 ደቂቃ | በወረዳዎች |
3. | ፍቺ | 22 ደቂቃ | በወረዳዎች |
4. | ሞት | 14 ደቂቃ | በወረዳዎች |
5. | ጉዲፈቻ | 19 ደቂቃ | በወረዳዎች |
6. | አባትነት በፍ/ቤት ማወቅ | 19 ደቂቃ | በወረዳዎች |
7. | ልጅነትን መቀበል | 19 ደቂቃ | በወረዳዎች |
8. | ልደት እድሳት፤ እርማት፤ ግልባጭ ማረጋገጫ አገልግሎት | 17 ደቂቃ | በወረዳዎችና(በክፍለከተማ) |
9. | ጋብቻ እድሳት፤ እርማት፤ ግልባጭ ማረጋገጫ አገልግሎት | 17 ደቂቃ | በወረዳዎችና(በክፍለከተማ) |
10. | ፍቺ እድሳት፤ እርማት፤ ግልባጭ ማረጋገጫ አገልግሎት | 17 ደቂቃ | በወረዳዎችና(በክፍለከተማ) |
11. | ሞት እድሳት፤ እርማት፤ ግልባጭ ማረጋገጫ አገልግሎት | 17 ደቂቃ | በወረዳዎች |
12. | ጉዲፈቻ እድሳት፤ እርማት፤ ግልባጭ ማረጋገጫ አገልግሎት | 17 ደቂቃ | በወረዳዎች |
2. የነዋሪዎች አገልግሎት
ተ.ቁ | የአገልግሎት ዓይነት | የሚወስደዉ ጊዜ | አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ |
1. | መታወቂያ አገልግሎት | 14 ደቂቃ | በወረዳዎች |
2. | ያላገባ አገልግሎት | 17 ደቂቃ | በወረዳዎች |
3. | ነዋሪነት ማረጋገጫ | 9 ደቂቃ | በወረዳዎች |
4. | መሸኛ | 13 ደቂቃ | በወረዳዎች |
5. | በህይወት ስለመኖር | 4 ደቂቃ | በወረዳዎች |
6. | ዝምድና ማረጋገጥ | 8 ደቂቃ | በወረዳዎች |
7. | ያላገባ እድሳት፤ እርማት፤ ግልባጭ ማረጋገጫ አገልግሎት | 14 ደቂቃ | በወረዳዎች |
8. | መታወቂያ እድሳት፤ እርማት፤ ግልባጭ ማረጋገጫ አገልግሎት | 9 ደቂቃ | በወረዳዎች |
9. | ባንክ ማረጋገጫ | 10 ደቂቃ | በወረዳዎች |
ከተገልጋይ የሚጠበቁ/ማሟላት የሚገባቸዉ መረጃዎች
1. የልደት ምዝገባ
የልደት ምዝገባ ለማከናወን መሟላት የሚገባቸው ደጋፊ ማስረጃዎች እና መስፈርቶች፡-
- ልደቱ የተከሰተዉ በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማስረጃ/ማሳወቂያ ቅፅ ማቅረብ አለበት፡፡
- ለውጭ ዜጎች ኢትዮጵያዊያን ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውንየልደት ማስረጃ ማቅረብ አለበት እንዲሁም በተመረጡ ወረዳዎች በመቅረብ ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የህጻኑ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ ልደቱን ለማስመዝገብ ሕጋዊ በፍርድ ቤት የተሰጠ የአሳዳሪነት/ሞግዚትነት ወይም ተንከባካቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ዕድሜው አስራ ስምንት ዓመትና በላይ የሆነ ግለሰብ ጊዜው ያላለፈበት የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የህጻኑ ወላጆች በህይወት ካሉ አባት እና እናት ሁለቱም ወይም ልደትን ለማስመዘገብ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ተገኝተዉ ልደቱን ማስመዝገብ ያልቻለ ወላጅ አባት ከሆነ ለህፃኑ ወላጅ እናት ልዩ የልደት ዉክልና በመስጠት እንዲሁም ተገኝተዉ ማስመዝገብ ያልቻለችዉ ወላጅ እናት ከሆነች ለህጻኑ ወላጅ አባት ልዩ የልደት ዉክልና በመስጠት ልደቱን ማስመዝገብ ይችላሉ፡
- ከወላጆች አንዱ በህይወት የሌለ እንደሆነ በህይወት ያለዉ ወላጅ የማችን ወላጅ ህጋዊ የሞት ማስረጃ ሲቀርብ ልደቱ ይመዘገባል
2. የጋብቻ ምዝገባ
የጋብቻ ምዝገባ ለማከናወን መሟለት የሚገባቸው ደጋፊ ማስረጃዎች እና መስፈረቶች፡-
- ተጋቢዎች ጋብቻ ለመፈፀም ማሰባቸውን እጅግ ቢዘገይ ጋብቻቸውን ለመፈፀም ከወሰኑበት ቀን ከአንድ ወር በፊት ለየክብር መዝገብ ሹሙ ማሳወቅ አለባቸው፡፡ሆኖም ይህ ድንጋጌ በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓት የሚፈፀም ጋብቻን አይመለከትም፡፡
- የጋብቻ ምዝገባ ቦታ ተጋቢዎች በጋራ የሚወስኑት ቦታ፣ ከተጋቢዎቹ አንዱ ይኖርበት የነበረው ቦታ ወይም ከተጋቢዎቹ የአንደኛው ወላጆች ወይም የቅርብ ዘመዶች የሚኖሩበት መደበኛ መኖሪያ ቦታ ይሆናል፡፡
- ሙሽዋዉ/ዋ ከዚህ በፊት አግብቶ/ታ የሞተችበት/ባት ከሆነ የሞት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፡፡
- የክብር መዝገብ ሹሙ ጥያቄው በቀረበለት ቀን ከተጋቢዎቹ ጋር በመነጋገር ከወሰነ በኃላ በማግስቱ ጋብቻው የሚፈፀምበትን ቀን በመግለጽ አመቺ በሆነው መንገድ ለ15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡
- ተጋቢዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጋቢ ምስክሮች አገልግሎቱ ያላለፈበት የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ ወይም የስደተኝነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ሌላ ማንነትን ሊገልፅ የሚችል ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጋቢዎች ከዚህ በፊት አግብተው የተፋቱ ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለባቸው፡፡
- ከ 6 ወር ወዲህ በተመሳሳይ ጊዜ የተነሱት ሁለት ሁለት 3 በ 4 የሆነ የተጋቢዎች ፎቶ-ግራፍ መቅረብ አለበት፡፡
- በባህላዊ ስርዓት የተፈፀመ ጋብቻ የተጋቢዎች ምስክሮች ወይም በጋብቻ ስርዓቱ ላይ የታደመ ሰው በክብር መዝገብ ሹሙ ፊት በአካል ቀርበው ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው፡፡
- በሙሽራው በኩል 2 በሙሽሪት በኩል 2 በድምሩ 4 ምስክሮች መቅረብ አለባቸው
3. የፍቺ ምዝገባ
የፍቺ ምዝገባ ለማከናወን መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች
- ፍቺው ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተፈፀመ መሆን አለበት፣
- የፍቺ አስመዝጋቢ ሆነው የሚቀርቡት ተፋቺዎች በጋራ ወይም ከተፋቺዎች አንዱ ወይም የተፋቺዎች ልዩ ውክልና ያለው መሆን አለበት፡፡
- ፍቺው በፍርድ ቤት የተከናወነ መሆኑን የሚገልፅ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
- ተፋቺዎች ፍቺውን ለማስመዝገብ ሲመጡ ጊዜው ያላለፈበት የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ ወይም ስደተኝነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ቀደም ሲል የጋብቻ ምስክር ወረቀት የተሰጠ ከሆነ መመለስ አለበት፡፡
4. የሞት ምዝገባ
የሞት ምዝገባ ለማከናወን የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- ሞቱን ለማስመዝገብ ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
- የሟች ማንነት የሚገልጽ ማሰረጃ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ መቅረብ አለበት፡፡
- ሞቱ የሚመዘገበው በግለሰቡ መጥፋት ውሳኔ ምክንያት ከሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
- ከሟች ጋር አብሮ ይኖር የነበረ ሰው ሟች መሞቱን ማስመዝገብ አለበት፡፡
- ከሟች ጋር አብሮ ይኖር የነበረ ሰው የሌለ እንደሆነ የሟች የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመዶች፣ እነዚህ የሌሉ እንደሆነ የቅርብ ጎረቤት ወይም ስለሟቹ መሞት የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ሟች መሞቱን ማስመዝገብ አለበት፡፡
- በአደጋ ወይም ባልታወቀ ምክንያት ሞቶ ማንነቱ ስላልታወቀ አስክሬን ሪፖርት የተቀበለ ፖሊስ ሪፖርቱ ከደረሰው ቀን በኋላ ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ ሞቱን ማስመዝገብ አለበት፡፡
- የመከላከያ ሠራዊት አባል በግዳጅ ላይ እያለ ከሞተ የክፍሉ አዛዥ በአገር መከላከያ ሚኒስቴር እንደ ክብር መዝገብ ሹም እንዲሠራ ለተመደበው ኃላፊ ሞቱን በማሳወቅ ማስመዝገብ አለበት፡፡
5. አባትነት በፍ/ቤት ማወቅ
የአባትነት በፍ/ቤት ማወቅ ምዝገባ ለማከናወን የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- አስመዝጋቢዉ የፍርድ ቤት ዉሳኔ ይዞ መቅረብ አለበት፡
6. ጉዲፈቻ
የጉዲፈቻ ምዝገባ ለማከናወን የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- ጉዲፈቻ የተደረገዉ ልጅ የቀድሞ የልደት ምስክር ወረቀት ካለዉ የምዝገባ ሂደት የሚስፈልጉ መረጃዎችን ክምስክር ወረቀቱ ከተወሰዱ በኃላ ለክብር መዝገብ ሹም መመለስ አለበት፡፡
- በፍርድ ቤት የፀደቀ የጉዲፈቻ ስምምነት ትክክለኛ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
7.ልጅነት መቀበል
የልጅነት መቀበል ምዝገባ ለማከናወን የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- አንድ ሰዉ በክብር መዝገብ ሹም ፊት በመቅረብ አባት መሆኑን በመግለፅ በሚሰጠዉ ቃል ወይም በጽሁፍ በሚያደርገዉ ኑዛዜ ወይም በሌላ በማናቸዉም ስልጣን በተሰጠዉ በለስልጣን በተረጋገጠ ሰነድ አማካኝነት አባት መሆኑን ማስመዝገብ ይቻላል ፡፡
8.መታወቂያ ለማዉጣት
አዲስ ለማዉጣት የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- በወረዳዉ ነዋሪ ቅጽ ላይ ተመዝግቦ መገኘት አለበት በተጨማሪ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ መቅረብ አለበት ፡፡
- የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነ እድሜዉ 18 አመት እና ከዚያ በላይ ሆኖት በቅጽ ላይ ተመዝግቦ የማይገኝ ከሆነ ለአገልግሎት ሲመጣ ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃ እና የሚያስመዘግበዉ የቤት ባለቤት ይዞ መገኘት አለበት፡፡
- ከአዲስ አበባ ዉጪ ይኖር የነበረ ግለሰብ ከነበረበት ቦታ የተማላ መረጃ ያለዉ መሸኛ በማምጣት በወረዳዉ ላይ አስመዝግቦ 6 ወር መጠበቅ እና ቅጹ ላይ የሚያስመዘግበዉ ሰዉ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
መታወቂያ ለማደስ የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- መታወቂያ አራት አመት ካለፈዉ ጊዜዉ ያለፈበትን መታወቂያ እና አንድ ፎቶግራፍ በመያዝ ማደስ ይችላሉ ፡፡
የጠፋ መታወቂያ ምትክ የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- ከፖሊስ ጣቢያ መጥፋቱን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለበት ፡፡
N.B፡-መታወቂያ በዉክልና አይሰጥም አይታደስም
9.ያላገባ ማስረጃ ለማዉጣት
ያላገባ ማስረጃ ለማዉጣት የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- አገልግሎት ጠያቂዉ የነዋሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተመዘገበ መሆን አለበት ፡፡
- የታደሰ እና ሙሉ መረጃ የያዘ የወረዳ ነዋሪነት መታወቂያ ዋናዉን ፎቶኮፒ ማቅረብ አለበት፡፡
- ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ጉርድ ፎቶ ግራፍ መቅረብ አለበት፡፡
- ተገልጋይ ቃለ መሃላ ፎርም ይሞላል ባለሙያዉም ቀጽ ላይ ካለዉ መረጃ አረጋግጦ ሰርተፍኬቱን ይሰጠዋል፡፡
ዉጪ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጲያዉያን የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- ከኢትዮጲያ ዉጪ የሚኖሩ ወይም ዜግነታቸዉን የቀየሩ ኢትዮጲያዊያን ያላገባ አገልግሎት ተገድቦ የሚሰጣቸዉ ከሀገርእስከወጡበት ጊዜ ተገድቦ ሲሆን ለዚህም ከኢትዮጲያ ሲወጡ የታተመላቸዉን ቪዛ ኮፒ እና የታደሰ ፓስፖርት ኮፒ መቅረብ አለበት ፡፡
- ዉጪ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ያልተገደበ ያላገባ ማስረጃ ማግኘት ሲፈልጉ ይኖርበት ከነበረ ሀገር አለማግባታቸዉን የሚገልጽ 6ወር ያላለፈዉ መረጃ በዉጪ ጉዳይ ሚኒስተር አረጋግጠዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶ ግራፍ መቅረብ አለበት፡፡
ያላገባ በዉክልና ለማዉጣት የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- ልዩ የዉክልና ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
- ዉክልናዉ ከዉጪ ሀገር የመጣ ከሆነ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት መመዝገብ መረጋገጥ አለበት፡፡
- የወካይም የተወካይም የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ኮፒ
- የወካይ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶ ግራፍ መቅረብ አለበት
- ተወካይ ፎርም ይሞላል ባለሙያው ቅፅ ላይ ካለው መረጃ አረጋግጦ ሰርተፊኬቱን ይሰጠዋል፡፡
N.B:- ያላገባ ሰርተፊኬት የሚያገለግሎው ለ6 ወር ብቻ ስለሆነ ከስድስት ወር በኃላ እንደአስፈላጊነቱ መታደስ አለበት
10.የመሸኛ አገልግሎት ለመውሰድ
መሸኛ አገልግሎት ለመዉሰድ የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣
- ከዚህ በፊት የወሰደውን የነዋሪነት መታወቂያ መመለስ አለበት
- የወሰደው መታወቂያ ጠፍቶ ከሆነ መጥፋቱን ፖሊስ ጣቢያ በማስመዝገብ የፖሊስ ጣቢያ ማስረጃ ወረቀት እና ማንነቱን የሚገልፅ ማስረጃ ይዞ መምጣት ጉዳዩን የሚገልፅ ማመልከቻ 4×4 ጉርድ ፎቶግራፍ ማቅረብ አለበት፡፡
11.መሸኛ መሟላት ያለባቸው ይዘቶች
- ባለመሸኛው(ባለጉዳዩ) ሙሉ ስም ከነአያት
- የእናት ሙሉ ስም
- የትውልድ ቀን፣ ወር እና ዓ.ም
- የትውልድ ቦታ
- የጋብቻ ሁኔታ
- መሸኛው የመጣበት ቦታ ሙሉ አድራሻ
- ብሔር እና ዜግነት
- ማህተም የተደረገበት ባለመሸኛው ፎቶ
- መሸኛን የሰጠው አካል ስምና ፊርማ
- መሸኛውን የሰጠው ተቋም የራስጌ እና የግርጌ ማህተም
- መሸኛው ወጪ የሆነበት ቀንና ቁጥር
12.ነዋሪ ስለመሆን አገልግሎት ለመውሰድ በሟላት ያለበት
- በነዋሪነት ቅጽ ላይ የተመዘገበ መሆን አለበት
- የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ዋናውና ኮፒ
- የማመልከቻ ፎርም መሙላት
13.በህይወት ስለመኖር አገልግሎት ለመውሰድ መሟላት ያለባቸው
- የወካይ ተወካይ የውክልና መታወቂያ ካርድ እና የታደሰ መታወቂያ ዋናው እና ኮፒ
- ማመልከቻ
- የአገልግሎት ክፍያ የለውም