
በጽ/ቤቱ ያሉት ስራ ሂደቶች(ዘርፎች)
- የፀጥታ መረጃ እና ግጭት አፈታት ጉዳዮች ስራ ሂደት
- የሰላም እሴት ግንባታ፤አደረጃጀቶችና ተቋማት ክትትልና ድጋፍ ስራ ሂደት
ራዕይ
በ2017 አዱስ አበባ ከተማ በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ፣ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ የሆነች ከተማ ሆና ማየት፤
እሴቶች
- ለላቀ ሰላምና ጸጥታ መትጋት
- ሚስጥር ጠባቂነት
- ፍትሐዊነት
- ሰብዓዊነት
- ታማኝነት
- ተጠያቂነት
- ተቋማዊ አጋርነት
- የህግ የበላይነትን ማክበርና ማስከበር
ተሌዕኮ
የተቀናጀ የጸጥታ ጉዳዮች አስተዳዳር እና የግጭት እቅድ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ወንጀልን በመከላከል፤ የሰላም እሴቶችን በመገንባት፣ በሃይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል መከባበርና መቻቻል እንዲሰፍን በማድረግ፤ የክትትል፤ ቁጥጥር እና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመዘርጋት፣ ነዋሪውንና ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ባቤትነት በማረጋገጥ ሰላም፣ ጸጥታና ደህንነቷ የተጠበቀ እና ህግና ስርዓት የተከበረባት ከተማ ማድረግ ነው፡፡
አድራሻ
የአቃቂ ቃለቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ ላይ ወለል 3 ቢሮ ቁጥር 305
በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልገሎቶች፡-
- የደንብ ማስከበር ጽ/ቤትን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
- የብሔራዊ የፀጥታና የሰላም ፖሊሲን መሠረት በማድረግ የክ/ከተማውን የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳይ ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ ከተማው አቀፍ ፖሊሲ ሲቀረጽ፤ ስትራቴጂ ሲነደፍ፤ ህግ ሲያመነጭ፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤
- በፀጥታ ጉዲዮች የከተማው አስተዲደር ዋና የፀጥታ አማካሪ ሆኖ ይሰራል፤ ለፀጥታና ሰሊም አስጊ የሆኑ ጉዲዮች ሊይ ተገቢ የሆነ አፋጣኝ እርምጃ ይወስዳል፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም እንደ አግባብነቱ ራሱ ወይም ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት የእርምት እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የግጭት መንስዔዎችን በጥናት ይለያል፣ ግጭት እንዳይከሰት ይከላከላል፤ ሲከሰትም ባህላዊና ዘመናዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ይፈታል፤
- በከተማው ልዩ ልዩ ሃይማኖትና ቤተ-እምነት ተከታዮች መካከል ሰላምና መከባበር እንዲሰፍን ለማድረግና ግጭትንም ለመከላከል እንዲቻል አግባብነት ካላቸዉ የፌድራሌም ሆነ የከተማው አስተዳደር አካላት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤
- በግጭት መከላከል፣ አያያዝም ሆነ አፈታት፣ በነዋሪው ደህንነት፣ ሰላም እና ፀጥታ አጠባበቅ ጉዳዮች ዙሪያ አግባብነት ካላቸው የፌድራል፣ የክልል፣ የከተማ አስተዳደር እና ሌሎች አካላት ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ያደርጋል፤ እንደአግባብነቱ ችግሮችን በተናጠል ወይም በጋራ ይፈታል፤
- ህግና ስርዓት መከበሩንና የህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት መጠበቁን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
- ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና በስውር የነዋሪውንና የመንግስትን ጥቅም ጉዳት ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና ድርጅቶችን በመከታተል ነዋሪውንና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፤
- ከጸጥታ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ቅሬታ እና አቤቱታዎችን ይቀበላል፤ ይመረምራል፤ እንዳግባብነቱ ራሱ ወይም በተጠሪ ተቋም ወይም በሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ቅሬታዎቹና አቤቱታዎቹ መልስ እንዱያገኙ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- በፌድራል መንግስት የተመዘገቡ እና ፈቃድና እድሳት የተሰጣቸውን የሃይማኖት ተቋማት እና የብዙሀን ማህበራት ለመረጃነት ይመዘግባል፤ መረጃ ያደራጃል፤ ህገ-መንግስቱንና ሌሎች ህጎችን አክብረው ስለመስራታቸው ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፤
- ለህግ አስከባሪ አካላት እና ለነዋሪዎች በወቅታዊ ጉዳዩች ዙሪያ አቅማቸውን በመገንባት የህዝብ አገልጋይነት ሚናቸውን እንዲወጡ ያልርጋል፤
- ሌሎች ህጎች ድንጋጌዎችና አሰራሮች እንደተጠበቁ ሆነው የጦር መሳሪያ ፈቃድ በሚመለከት የትብብር ደብዳቤ ይሰጣል፤ መረጃ ያደራጃል፤ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፤
- በከተማው የጦር መሣሪያ አጠቃቀምና አያያዝ በተመለከተ የምዝገባ አፈጻጸምን ይከታተላል፤
- የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ወንጀል፣ የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ሕገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈፀሙ የማስተባበር ስራዎችን ይሰራል፤ ተፈጽሞ ሲገኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል
- የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት በህብረተሰብ ተሳትፎ ላይ እና በመስፈርቱ መሰረት ስለመከናወኑ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፤
- የፀጥታ አስተዲር እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍልች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- የፀጥታ ሁኔታ መረጃ ይሰበስባል፣ ያደራጃል፣ ጥናትና ምርምር ያደርጋሌ፣ ውጤቱን ለሚመሇከተው አካል ያቀርባል፤ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት ተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤
- የመንግስትና የግል ተቋማትን እና ነዋሪውን በአካባቢያቸው የፀጥታ፣ ሰላም እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉበትን ስሌት ይቀይሳል፤ ተቋማዊ አደረጃጀት ይፈጥራል፤ ያስተባብራል፤
- በክ/ከተማው ክልል ውስጥ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የጉዳቱ መጠን እንዲይባባስ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፤ በአደጋው ክልል ውስጥ የሚገኙ ማህበረሰብ አካላት የህይወትና የንብረት ደህንነት እንዲጠበቅ ያርጋል፤
- ስለሰላማዊ ሰልፍ፣ በአደባባይ ሊይ ስለሚከናወኑ የተለያዩ ፕሮግራሞች እና ስብሰባዎች ከዋና ስራ አስፈጻሚን ያማክራል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- የመንግስትና የግል ተቋማት እንዱሁም የአካባቢ ቅጥር ጥበቃ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
- የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት አደረጃጀትና አሰራር አጥንቶ ለዋና ስራ አስፈጻሚ ያቀርባል፤ ሲወሰንም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- 1.ጥናትና ምርምር ማድረግ
- ስልጠና መስጠት
- የሰላም ዕሴት መገንባት
- የጦር መሣሪያ አጠቃቀምና አያያዝ ምዝገባ አፈጻጸም ክትትል
- ሰላማዊ ሰልፍ፣ የአደባባይ ላይ ኩነቶችና ስብሰባዎች አፈጻጸም መከታተል
- ማህበረተሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ክትትልና ቁጥጥር
- የመንግስትና የግል ተቋማት ቅጥር ጥበቃ ክትትልና ቁጥጥር
- ከጸጥታ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ቅሬታ እና አቤቱታዎች መቀበልና ምላሽ መስጠት
- የፀጥታ መረጃ አገልግሎት
10 .የፀጥታ ስጋቶች መለየትና ወንጀል መከላከል
- የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ፈጣን ምላሽ መስጠት
- ለፀጥታና ደህንነት አስጊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰድ
- የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማጎልበት
14.የሃይማኖት ተቋማት እና የብዙሃን ማህበራት መመዝገብና ማደራጀት ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስክ ስትራቴጂያዊ ውጤት የጸጥታ አስተዳደር ደህንነቷ የተጠበቀና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ የሰላም ግንባታ የዳበረ እሴትና አብሮነት የሰፈነባት ከተማ በህብረተሰብ ተሳትፎ አስተማማኝ ሠላም ማስፈን
- ለሃይማኖት ተቋማትና ማህበራት ድጋፍ ደብዳቤ መጻፍ
- የሰላምና ጸጥታ አደረጃጀቶችን ማደራጀትና ማጠናከር
- ከባለድርሻ አካላት ጋር የቅንጅት ስራዎችን ማከናወን
10.ተገልጋዮች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝና በአካል በመቅረብ የሚፈልጉትንና ፅ/ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎት መጠየቅ ይችላሉ፡፡