ንግድ ፅ/ቤት

ራዕይ (Vision)

በ2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ የንግድ ማዕከል ከሆኑ የአፍሪካ ከተሞች ግንባር ቀደም ከተማ ሆና ማየት፡

 

እሴቶች (Values)

  • ቅንነት
  • ግልፀኝነት
  • ተጠያቂነት
  • ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት
  • በእዉቀትና በእምነት መስራት
  • ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት
  • ሁል ጊዜ ከተግባር መማር

 

 

ተልዕኮ (Mission)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ህብረተሰብ ተሳትፎ በማጠናከር፣ በዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጅ በመታገዝ እና የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አሰራር በማዘመን፣ ደረጃዎችን የጠበቁ የግብይት ማዕከላትን በማስፋፋት፣ ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት እና የሸማቾችን መብትና ጥቅም በማስጠበቅ ፍትሃዊ ግብይትን ማስፈን፤

የተቋሙ ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት

  1. የህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲን በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፣
  2. የንግድና ገበያ ልማት ተወዳዳሪነትን በቀጣይነት የሚያረጋግጡ ከተማ አቀፍ ፖሊሲዎችን ይቀርፃል፣ በሚመለከተው አካል ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፣
  3. የክፍለ ከተማው የምርት ውጤቶች እንዲታወቁ ያደርጋል፣ አውደ-ርዕይ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ይሳተፋል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፣
  4. የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በክፍለ ከተማው ውስጥ በንግድና ገበያ ልማት ስራ ላይ በሰፊው እንዲሰማሩ ያበረታታል፣ የቴክኒክና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል፣ በንግድ ስራ ለሚሰማሩና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ለሚያቋቁሙ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች የንግድ ፍቃድ ይሰጣል፣ይቆጣጠራል፣
  5. የክፍለ ከተማውን የንግድ መዝገብ ይሰጣል፤ የንግድ ስም ምዝገባ ያከናውናል፤ ያስተዳድራል፤ የንግድ ማህበራትን በህግ መሠረት በመመዝገብ ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ያግዳል፤ ይሰርዛል፤
  6. በሕግ ለሌላ አካል የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በክፍለ ከተማው ውስጥ የመሠረታዊ ንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ስርጭት የገበያ ህግና ስርዓትን መከተሉን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  7. ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶችና አገልግሎቶች ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲወገዱ ያደርጋል፤
  8. የፍጆታ ምርቶችን የአገልግሎት ዘመንና የተዘጋጁባቸውን ንጥረ-ነገሮች ይዘት ሸማቹ ማወቅ በሚችልበት ሁኔታ መሆኑን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  9. በገበያው ውስጥ በቂ አቅርቦት መኖሩንና ግዥና ሽያጩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ለነጻ ገበያ ውድድር እንቅፋት የሆኑ ድርጊቶችና ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ስራዎች እንዳይፈጸሙ በመከላከልና በማስወገድ የከተማውን ነዋሪዎች ጥቅም ያስጠብቃል፤
  10. የገበያ ዋጋ መረጃ የመሰብሰብ፣ የመተንተን እና የማቀነባበር ተግባራትን ያከናውናል፤ እንዳስፈላጊነቱ በጥቅም ላይ ያውላል፤
  11. የልኬት መሳሪያዎችንና መስፈሪያዎችን ትክክለኛነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤ ትክክለኛ ሆነው ያልተገኙ የልኬት መሳሪያዎችንና መስፈሪያዎችን እንዲወገዱ ያደርጋል፤
  12. ለገበያ አገልግሎት እንዲውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን ይቆጣጠራል፤ ያስተዳድራል፤ የአገልግሎት አስጣጡን በተመለከተ መመሪያ ያወጣል፤
  13. ኢ-መደበኛ ንግድ ወደ መደበኛ ስርዓት የሚገባበትን አሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
  14. ሕገ-ወጥ ንግድን ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡