Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.

የተቋሙ ሥልጣንና ኃላፊነት

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 74/2014 የተሰጡ ሥልጣንና ኃላፊነት

  • ከመንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ማሰልጠኛ ኮሌጆች ጋር በትብብርና በመደጋገፍ ይሰራል
  • የክፍለ ከተማዉን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎችን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
  • የተቋሙን ተልዕኮ ሊያሳኩ የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን ያካሂዳል፤ ያስተዋውቃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
  • የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አሠልጣኞች እና ቴክኒሺያኖችን የክህሎት ክፍተት በመለየት በክህሎትና በቴክኖሎጂ ብቃት ለማሳደግ አጫጭር ስልጠና የሚያገኙበትን ሥልት ያመቻቻል፤
  • መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞችና የግል አመልካቾች የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የሚያገኙበትን አሰራር ያመቻቻል፤
  • በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ መሰማራት የሚፈልጉትን የግል ባለሀብቶችን ይደግፋል፤ መንግስታዊ ከሆኑ እና ካልሆኑ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ይፈጥራል፤
  • የኢንተርፕራይዞችና ኢንዲስትሪዎች ምርታማነትና ተወዳዳሪነት የሚያጎለብቱበት አገር በቀል ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን ይደግፋል፤ ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፡፡
  • ማሰልጠኛ ተቋማት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተሟላ የኢንዲስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ እንዲሰጡ ያስተባብራል
  • የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ልዩ ፋላጎት ያላቸውና ሌሎች ትኩረት የሚሹ ዜጎች ትኩረት እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ በዚህ ረገድ የሚቀየሱ አገር አቀፍ ሥርዓቶች ተግባራዊ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፤
  • የቴክኒክና ሙያ ምሩቃን በሙያቸው ተደራጅተው ወደ ሥራ በሚገቡበት ጊዜ ያላቸውን የሙያ ክፍተት በመለየት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በየደረጃው ሙያዊ እገዛ እንዲደረግላቸው አስፈላጊውን የሥራ ትብብር ያደርጋል፤
  • የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠናን አስመልክቶ ለሕብረተሰቡ የተለያዩ የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረኮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጃል፤ ያስተባብራል፤ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡
  • የአስተዳደሩን ተቋማት የኮምፒውተር መረቦችና አፕሌኬሽኖች እንዲቀናጁና እንዲናበቡ ያደርጋል፤ ያረጋግጣል፤አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለማዘመን በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ያደርጋል፤ ቀጣይነቱን ያረጋግጣል፤
  • የአስተዳደሩን ተቋማት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖልጂ መሰረተ ልማት ክፍተትን ይለያል፤ አስፈላጊ መስፈርቶችን በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤ ሲፈቀድም ይዘረጋል፤ እንዲዘረጋም ያደርጋል፤
  • የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአስተዳደሩ የሚሰጡ አገልግሎቶች አንድ መሀከል የመረጃ ቋት ያደራጃል፤ ያስተዳድራል፤ ቀጣይነቱን ያረጋግጣል፤
  • በአስተዳደሩ ባሉ ተቋማት የካይዘን ፍልስፍናን በማስተግበር አሰራራቸዉን አዘምነዉ ቀልጣፋና ዉጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ እና ምርትና ምርታማነትን እንዱያሳድጉ የሚያስችል የሙያ ድጋፍ ያደርጋል፣ ይከታተላል፤ ቀጣይነት ያለዉ መሻሻል መኖሩን ያረጋግጣል፤
  • በግል አምራች ድርጅቶች የካይዘን ፍልስፍናን እንዲተገብሩ ተገቢ የሚሆኑ ተቋማትን በትብብር ይለያል፣ የግንዛቤና ሙያዊ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ የሙያ ድጋፍ ያደርጋል፤
  • የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተደራሽነትና ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ይከታተላል፤ይደግፋል፡፡
  • በመንግስትና በግል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ለሚሰማሩ ወይም ፕሮግራም ለሚያስፋፉ በስታንዳርዱ መሰረት ያላቸውን ዝግጅት ሱፐርቪዥን በማካሄድ ይገመግማል፤ ጉድለቶቻቸውን እንዲያርሙ አቅማቸውን ይገነባል፤ ዕውቅና ለሚሰጠው አካል መረጃ ይሰጣል፤ ይቀበላል፤ ብቃታቸውን ለማሳደግ ይሰራል፡፡

ራዕይ /Vision/

በአስተዳደሩ ያሉ ተቋማት በ2017 ዓ.ም ምርታማነታቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በማሻሻል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ማየት

ተልዕኮ /Mission

 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በውጤት ተኮር ስልጠና ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት፣ የኢንዲስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍና የቴክኖሎጂ ምርምርና ሽግግር አገልግሎቶችን በመስጠት፣ ጥራትና ደህንነቱ የተጠበቀ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት እና የኢንፎርሜሽን ሲስተም በማልማት፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና የካይዘን ፍልስፍናን ተግባራዊ በማድረግ የተቋማትን የምርት ጥራትና አገልግሎት በማሻሻል የክፍለ ከተማዋን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፡፡

.እሴት /values/ 

  • መማር
  • ትብብር (Collaboration)
  • ልህቀት (Excellence)
  • ለለውጥ ዝግጁነት
  • ያልተገደበ አስተሳሰብ
  • ለትውልድ የሚሸጋገር መሰረት

ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች

ውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና

ውጤት፡ ብቁ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል

ጥራት ምርታማነትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን

ውጤት፡ ተወዳዳሪና ዉጤታማ ኢንዱስትሪዎች

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት

ውጤት፡ ደረጃውን የጠበቀ የኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና ሲስተም ተደራሽነት

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦፕሬሽንና አገልግሎት

ውጤት፡ ቀልጣፋና ቀጣይነት ያለው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት


  በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች

  • በክፍለ ከተማ ደረጃ በአራት ቡድን 27 ዋና ዋና አገልግሎቶች ይሰጣሉ፡፡
  • ከተገልጋይ የሚጠበቅ

    • ቴክኒካል ድጋፍና የምክር አገልግሎት/የአገልግሎት ጥያቄ በደብዳቤና በተዘጋጀዉ ቅፅ መሠረት ኦን ላይን /10.23.19.25፡8080/ መጠየቅ
    • ስለ አገልግሎቶቹ ሙሉ መረጃ መጠየቅና መጠቀም እና ማብራሪያ ማግኘት
    • ሕጎችን እና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
    • አገልግሎት ለማግኘት ትክክለኛና የተሟላ መረጃ ማቅረብ
    • የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታን መከተልና ሟሟላት
    • ለካይዘን ትግበራ ምቹ ሁኔታ መፍጠር
    • በትግበራ ላይ ትብብር ማድረግ፤ ባለቤት መሆንና መከታተል፤
    • የተቋማትን የቴክኖሎጂ ትግበራ ግልፅ ሪፖርት ማቅረብ
    • የተዘረጉ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በአግባቡ መጠቀምና መጠበቅ/ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀምና ማስቀጠል/
    • ..የበቁ ሰልጣኞችን ከስራ ጋር ማሰተሳሳር
    • .የስራ እድል ለሚፈጠርላቸዉ ለስራ ፈላጊዎች አጫጭር ስልጠና እንዲሰጥ የሥም ዝርዝር መረጃ በአርድና በሶፍት ኮፒ በደብዳቤ ማስገባት
    • የቴክኒክ ሙያ ተቆማት ገበያ ፍላጎት ጥናት ትክክለኛ ወቅታዊና ተገቢነት ያለው መረጃ መስጠት
    • የቴክኒክ ሙያ ተቆማት የወር፤የሩብ ዓመትና የዓመት ሪፖርት ማቅረብ

1.የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተልማት ማኔጅመንትና ጥገና ቡድን

በዚህ ቡድን ስር 12 ዋና ዋና አገልግሎቶች ይሰጣሉ እነሱም፡-

1.የዳታ ማዕከልና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት

2.ሲስተም (ሰርቨር) ማኔጅመንት

3.ኢ-ሜይል አገልግሎት

4.አክቲቭ ዳይሬክተሪ አገልግሎት

5.ቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት

6.ኔትዎርክ ማኔጅመንት

7.ኢንተርኔት አገልግሎት ማኔጅመንት

8.የኢንፎርሜሽን ሲስተም ጥበቃ ማድረግ

9.በኢንፎርሜሽን ሲስተም ደህንነት ችግሮች ላይ እርምጃ መውሰድ

10.በኢንፎርሜሽን ሲስተም ላይ የተከሰቱ ጉዳቶችን መመለስ

11.ኣይቲ ሰፖርት

12.የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማትና ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች ጥገናና እድሳት

2.ፍትዌር ሲስተም ማኔጅሜንት ቡድን

በዚህ ቡድን ስር 3 ዋና ዋና አገልግሎቶች ይሰጣሉ እነሱም፡-

1.ሶፍትዌር ማኔጅመንት

2.ዌብ-ሳይት/ፖርታል ማኔጅመንት/

3.ዳታ-ቤዝ ማኔጅመንት

 

3.የግል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትን ማብቃት ቡድን

በዚህ ቡድን ስር 8 ዋና ዋና አገልግሎቶች ይሰጣሉ እነሱም፡-

1.የውጤት ተኮር ስልጠና አሰጣጥ ሂደትን በመፈተሸ ድጋፍ ማድረግ፣

2.የሱፐርቪዥን ድጋፍ መስጠት፣

3.የፕሮግራም ማደስ ፣ማስፋፋት እና ዕውቅና የማግኘት አቅማቸውን ማሳደግ፣

4.በህዝብ ንቅናቄ፣በቴክኖሎጂና ክህሎት ውድድር እንዲሳተፉ መደገፍ፣

5.በተቋማትና ሰልጣኞች ያሉ አለመግባባቶች በጋራ እንዲፈቱ ማድረግ፣

6.ከኢንዱስትሪውና ባለድርሻ ጋር ትስስር በመፍጠር የውጤት ተኮር ስርዓቱን ማጎልበት፣

7.ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ ስርአት መዘርጋትና ማስተዳደር፣

8.የአለም አቀፍ ደረጃ መስፈርትን እንዲያሟሉ ድጋፍ ማድረግ፣

4.የካይዘን ሽግግርና ልማት ቡድን

በዚህ ቡድን ስር 4 ዋና ዋና አገልግሎቶች ይሰጣሉ እነሱም

1.ተቋማትን ለትግበራ ማዘጋጀት

2.የማስተግበሪያ ስልጠና (የግንዚቤ ፣ ቴክኒካል ስልጠና፣ የአሰልጣኞች)

3.የትግበራ ማማከር

4.ቴክኒካል ድጋፍ