
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽህፈት ቤት
ራዕይ /vision/
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማን በ2017 ዓ/ም ከተማዋን የሚመጥኑና የህዝቡን ፍላጎት ሊያሟሉ የሚችሉ ወጪ ቆጣቢ ዲዛይኖችን በማዘጋጀት የመንግስት ህንጻዎችን ገንብቶ ለነዋሪዎቿ ተደራሽ ማድረግ፤
ተልዕኮ /mission/
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማን ስታንዳርዱን በጠበቀ ወጪ ቆጣቢ ዲዛይን መሠረት የመንግስት ህንጻዎችን ገንብቶ ተደራሽ በማድረግ ለክ/ከተማው ነዋሪዎች ምቹና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት፡፡
ዕሴቶች /values/
- ግልጽነት!
- ተጠያቂነት!
- ፍትሃዊነት!
- ለለውጥ ዝግጁነት!
- ጥራትና ወጭ ቆጣቢነት!
- ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት!
- ቅድሚያ ለደህንነት (Safty First)!
ጽ/ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ፡-
አቃቂ ቃሊቲ ክፍከ ከተማ አስተዳደር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202.
– ኢሜይል፡ info@ akakiconstructionoffice.com
– ቴሌግራም አድራሻ፡- Akaki Kality Sub City, Design & Construction Works Office.

በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች ብዛትና ዝርዝር
- ለአማካሪ እና ለስራ ተቋራጭ የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት፣
- ጨረታ ማውጣትና አሸናፊውን መለየት፣
- የውለታ ሰነድ ማዘጋጀት፤
- ከየተቋማቱ የሚቀርበውን ፍላጎት መሠረት በማድረግ የግንባታ ዕቅድ ማዘጋጀት፣
- የፕላን ስምምነት ከሚመለከተው አካል ማውጣትና ተግባራዊ ማድረግ፤
- የግንባታ ፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት ማዘጋጀት፣
- ዲዛይኖችን በስታንዳርዱ መሰረት ማዘጋጀት (ውስብስብ ያልሆኑና የህንጻ ከፍታቸው ከጂ+1 ያልበለጡ)፤
- ለተዘጋጀ ዲዛይን የግንባታ ፈቃድ ማውጣት፤
- የተዘጋጀውን ዲዛይን በስታንዳርዱ መሰረት መዘጋጀቱን ማረጋገጥ፣
- የመንግስት ግንባታዎችን ውለታ ማስተዳደር፤
- በውሉ መሰረት ባልተፈጸሙ ግንባታዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ማስወሰድ፣
- የግንባታ ርክክብና መሰረተ ልማት እንዲሟላ ክልትትል ማድረግ፤
- ዘመናዊ መራጃ አያያዝ ስርዓት መዘርጋት፤
- የክዋኔና ፋይናንሽል ኦዲት ማከናወን፤
- ከግንባታዎች ጋር የተያያዙ የሚቀርቡ ቅሬተዎችን መቀበልና መፍታት፤
ከተገልጋይ የሚጠበቅ ማሟላት ያለባቸው ዝርዝር ሁኔታዎች፡-
- የዲዛይን ጥያቄ መረጃ ማቅረብ፤
- ለኦዲት ከሚመለከተው አካል ፍቃድ /ትዕዛዝ/፤
- የግንባታ ፍላጎታቸውን በጽሁፍ ማቅረብ፤
- በፕሮጄክት ግምገማ ወቅት ጥሪ ሲደረግላቸው መገኘት፤
- በሚወጡ ጨረታዎች ላይ ጥሪ ሲደረግላቸው መሳተፍ፤
- በህግ ማስከበር ሂደት ላይ መተባበር፤
- ግንባታው ሲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ማቅረብ፤