
በጽ/ቤቱ ስር ያሉ ቡድኖች
- የቱሪዝም ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ቡድን
- የኪነ ጥበብ ሀብቶች ልማት መድረኮች እና ኩነቶች ዝግጅት ቡድን
- ቤተ መፃህፍት አገልግሎት አሰጣጥ ቡድን
- የኪነ-ጥበብ ኢንዱስትሪ ማበልጸግና ማስፋፋት ቡድን
- የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ብቃት ማረጋገጥ ቡድን
- የባህል እሴት እደጥበብ ሀብቶች ልማት ቡድን
ራዕይ (Vision)
የክ/ከተማችንን ሕዝብ ባህላዊ፣ ኪነ ጥበባዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ መስህቦችን በማጥናት፣ በመጠበቅ፣ በማልማት፣ በማስተዋወቅና ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ እና የክ/ከተማችንን መልካም ገጽታ በመገንባት ዘላቂ የሆነ ፣ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ፣
ተልዕኮ (Mission)
በ2022 የባህል፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ዘርፍን በማላቅ ከቀዳሚ የክ/ከተማችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና መሠረቶች አንዱ ማድረግ
እሴቶች (Values)
- ብዝሀነትን ማክበር
- እንግዳ ተቀባይነት
- ግልጸነት
- ተጠያቂነት
- ለለውጥ ዝግጁነት
- የላቀ አገልግሎት
- አሳታፊነት
- ሙያዊ ብቃትን ማሳደግ
አድራሻ
አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንጻ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር ……..
የጽ/ቤቱ ዋና ዋና አገልግሎቶች
በባህል ዘርፍ፤ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ዘርፍ
- የባህል አገልግሎቶች የሙያ ብቃት(ማረጋገጥ/ጫ) መስጠት ፣ ማደስ ፣ቁጥጥርና ክትትል ስርዓት መዘርጋት፣
- የባህል እሴቶችን የማሳደግ፣ የማስተዋወቅና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን፣እንዲሁም መጤ ባህሎችን የመከላከል አገልግሎት፣(መስጠት)
- ከባህል ዕደ-ጥበቦች አንጻር አገራችን ከዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንድታገኝና በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎችም ገቢ እንዲያገኙ፤ እንዲሁም ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር ስልጠና የማመቻቸትና የማስተዋወቅ ተያያዥነት ያላቸውን አገልግሎቶች መስጠት፣
- በከተማችን የሚገኙ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ማጥናት፣ ማልማት፣ መንከባከብና እድሳት እንዲያገኙ ማድረግ፤እንዲሁም የምዝገባ ስርአት መዘርጋት ፡፡
- አዲስ አበባ ከተማን የቱሪዝም መዳረሻ ከማድረግ አንጻር የቱሪስት መስህቦችን ማልማትና እንዲሁም በከተማው ውስጥ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ፤ብሎም ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን ማረጋገጥ፡፡
- ለቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሙያ ብቃት(ማረጋገጥ/ጫ) መስጠት፣ ማደስ፣ በአገልግሎቶች አሰጣጥ ላይ የቁጥጥርና ክትትል ስርአት በመዘርጋት የአገልግሎቱ ጥራትና ተደራሽነትን፣ ህጋዊነትን ማረጋገጥ፡፡
- ከተንቀሳቃሽ ቅርሶችና ከሙዚየም ጋር በተያያዘ ለታሪክ አጥኚዎችና ለጎብኚዎች አገልግሎት መስጠት፡፡
- ለተማሪዎች ብሎም ለከተማዋ ነዋሪዎች፣ የቤተ መፃህፍት የንባብ ፣ የውሰትና የሪፈረንስ አገልግሎት መስጠት አገልግሎቱንም በማዘመን በአይ.ሲ.ቲ የታገዘ ማድረግ/አገልግሎት መስጠት፡፡
- ለከፍተኛ አመራሮችና በተለያየ እርከን ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች የልዩ ቤተመፃህፍት አገልግሎት መስጠት፡፡ይኸውም የንባብ ፣ የውሰትና የሪፈረንስ አገልግሎት፤በሌላ መልኩም ከአመራሩ ጋር አብሮ የሚሄድ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ማድረግ፡፡
- የሴቶችንና፣ ወጣቶችን ፖለቲካዊ፤ኢኮኖሚያዊና፣ ማህበራዊ ተጠቃሚነትን
የሚያረጋግጡ የኪነ-ጥበብ ውጤቶችን በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፡፡
- ህፃናትን የሚገነቡና ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያስችሉ፤የኪነ-ጥበብ ውጤቶችን በማዘጋጀት ለተገልጋዩ ተደራሽ ማድረግ፡፡
በኪነ-ጥበብ ዘርፍ የሚካተቱ አገልግሎቶች፤
- የኪነ-ጥበብ ክበብ ማደራጀት ስራ መስራት፣
- በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት ሙያዊ ሥልጠና መስጠት፣
- የኪነ-ጥበብ አዲስ የብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠት፣
- የኪነ-ጥበብ የሙያ ብቃት እድሳት አገልግሎት መስጠት፣
- የተደራሽ የኪነ-ጥበብ መረጃዎችን አገልግሎት መስጠት፣
- የኪነ-ጥበባት የሱፐርቪዥን አገልግሎት መስጠት፣
- የኪነ-ጥበብ ከተማ አቀፍ ኩነቶችን ማስተባበር አገልግሎት መስጠት፣
- የስነ-ጽሁፍ ምሽት አገልግሎት መስጠት፣
- የኪነ-ጥበብ የዕይታዊ ጥበባት ኤግዚቪሽን ማዘጋጀት፣
በቱሪዝም ዘርፍ የሚካተቱ አገልግሎቶች፣
- የቱሪዝም አገልግሎቶች፣ ገበያ ጥናት (መስህቦችን፣ አገልግሎቶችን ማጥናት መረጃዎችን የማቅረብ አገልግሎት መስጠት፣
- የከተማውን የቱሪዝም ስታስቲክስ በመሰብሰብ፣ በመተንተን፣ በማደራጀት የመረጃ አገልግሎት መስጠት፣
- የከተማውን የቱሪዝም ሀብቶች በህትመትና በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ማሰራጨትና ማስተዋወቅ፣
- የከተማውን የቱሪዝም ሀብቶች በተለያዩ ኤግዚቪሽን ላይ በማሳተፍ ማስተዋወቅና የቱሪዝም ገበያ ሲምፖዚየም ማዘጋጀትና ገበያ መፍጠር፣